የሕንድ ዝርያ ያላቸው አሜሪካውያን ዳኞች የትራምፕን የገንዘብ ዕገዳ በማቆማቸው ጥቃት እየሰነዘሩባቸው መሆኑ ተነገረ

በትራምፕ አስተዳደር ስር የሚገኘው የጤና እና የሰብዓዊ አገልግሎት መሥሪያ ቤት በቅርቡ አምስት በዴሞክራቶች የሚመሩ ግዛቶች የሚያገኙትን ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የፌዴራል የድጋፍ ገንዘብ ለማገድ ወስኖ እንደነበር ይታወቃል።

ይሁን እንጂ በኒው ዮርክ የፌዴራል ዳኛ የሆኑት አሩን ሱብራማኒያን ይህንን ውሳኔ ለ14 ቀናት የሚያቆይ ጊዜያዊ ትእዛዝ  አውጥተዋል።

የትራምፕ አስተዳደር ዕገዳውን የጣለው በሜኔሶታ ግዛት ውስጥ በሚኖሩ ሶማሊያውያን ስደተኞች አማካኝነት “ከፍተኛ የገንዘብ ምዝበራ እየተፈጸመ ነው” በሚል ምክንያት ቢሆንም፣ ዳኛ ሱብራማኒያን ግን ውሳኔው በዝቅተኛ ገቢ የሚኖሩ ቤተሰቦች ላይ ሊጠገን የማይችል ጉዳት ያደርሳል በሚል ዕገዳው እንዲቆም አድርገዋል።

ይህንን ውሳኔ ተከትሎ፣ የትራምፕ ደጋፊዎች በሆኑት የ”MAGA” ንቅናቄ አባላት አማካኝነት በዳኛው ላይ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ከፍተኛ የዘረኝነት እና የጥላቻ ጥቃቶች እየተሰነዘሩባቸው ይገኛል።

ዳኛው የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ቢሆንም፣ “ከአገር ይውጡ” እና “ለሕንድ ወግነዋል” የሚሉ አስተያየቶች በስፋት እየተሰነዘሩ ነው። በተመሳሳይ መልኩ ዳኛ ኢንዲራ ታልዋኒ (Indira Talwani) የትራምፕ አስተዳደር ከኩባ፣ ሄይቲ፣ ኮሎምቢያ እና ሌሎች አገራት የመጡ 12,000 የሚጠጉ ስደተኞችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚያገናኘውን ፕሮግራም ለማቋረጥ ያቀደውን ውሳኔ በማገዳቸው ተመሳሳይ ጥቃት እየደረሰባቸው ነው።

እነዚህ ዳኞች የትራምፕን አስተዳደር ፖሊሲዎች በሕግ አግባብ በመሞገታቸው ምክንያት የሚሰነዘርባቸው ጥቃት፣ በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥላቻ እየጨመረ መምጣቱን እንደሚያሳይ የዜና ዘገባው አመልክቷል።

በተለይ በሜኔሶታ ሶማሊያውያን ላይ የሚሰነዘረው የወንጀል ክስና ይህንን ተከትሎ የሕንድ ዝርያ ባላቸው ዳኞች ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት፣ አገሪቱ ያለችበትን የፖለቲካ ውጥረት ይበልጥ አባብሶታል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories