በኢራን የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የአገሪቱ መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንዲያቆም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራንን ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህንን ተከትሎ ከኢራን ጋር የንግድ ግንኙነት ባላቸው አገራት ላይ የ25 በመቶ ታሪው እንደሚጣል ነው ያስታወቁት፡፡
ከኢራን ጋር ከ100 በላይ ሀገራት የሚገበያዩ ሲሆን ቻይና፣ኢራቅና የተባበሩት አረብ ኤምሬት በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡
የኢራን የጉምሩክ አስተዳደርን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ያሰራጨው መረጃ እንደሚያሳየው ቻይና እ.ኤ.አ. በጥቅምት 2025 ከኢራን ከ14 ቢሊየን ዶላር በላይ ምርቶችን ስትገዛ ኢራቅ 10.5 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ሸቀጦችን ወደ አገሯ አስገብታለች፡፡@SECO


