ስታርፔይ የኤግልላይን ቴክኖሎጂ እህት ኩባንያ ሲሆን በንግድ ባንክ በኩል የሚፈፀሙ ክፍያዎችን ማሳለጥ የሚያስችል የክፍያ ስርዓት እንደሆነ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ተወካይና የኮርፖሬት አገልግሎቶች ተቀዳሚ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ በዘርፉ ይሰጡ የነበሩ አገልግሎቶች ወቅቱን በዋጀ የዲጂታል መተግበሪያዎች እየተተኩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
የዲጂታል ትግበራ በተናጠል መንቀሳቀስን ሳይሆን ትብብር እንደሚያስፈልግ ጠቁመው የዲጂታል 2030 ግብን ለማሳካት መተባበር አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።
ይፋ የተደረገው የስታርፔይ ስርዓት ለደንበኞች የሚቀርቡ አገልግሎቶች የተገልጋዩን ፍላጎት ለማሟላት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል።
የኤግላይንስ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በርሱፈቃድ ጌታቸው ስታርፔይ ነጋዴዎች በቀላሉ ክፍያዎቻቸውን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለመሠብሠብ እና ሌሎች በርካታ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
ስታርፔይ ነጋዴዎች ከደንበኞቻቸው ከየትኛውም የገንዘብ ተቋም የተፈፀመ ክፍያን በቀላሉ ማረጋገጥ የሚችሉበት መተግበሪያ መሆኑን አስታውቀዋል።
ነጋዴዎች የኢንተርኔት አገልግሎት ወይም ስማርት ስልኮች ሳያስፈልጋቸው ክፍያ መፈፀሙን የሚያረጋግጡበት አሰራር እንዳለውም ጠቁመዋል።
ነጋዴዎች የክፍያ መፈፀምን ለማረጋገጥ የሚገጥማቸውን ፈተናና በተለያዩ የገንዘብ ተቋማት የሚፈፀምን የተበታተነ የክፍያ ስርዐት ተግዳሮትን የሚያስቀር መሆኑንም ገልጸዋል።@SECO


