ካናዳ እና ቻይና የታሪፍ ቅነሳ ስምምነት ማድረጋቸው ተነገረ

​የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ በቤጂንግ ከፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር ባደረጉት ከፍተኛ ውይይት፣ ሁለቱ አገራት ላለፉት ዓመታት በንግድ ላይ ጥላውት የነበረውን የታሪፍ ጫና ለመቀነስ ተስማሙ። ይህ ስምምነት ካናዳ ከዋነኛ የንግድ አጋሯ አሜሪካ ጋር በታሪፍ ምክንያት የገባችውን ውጥረት ተከትሎ፣ የንግድ አማራጮቿን ለማስፋት የወሰደችው ስትራቴጂካዊ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።

 በስምምነቱ መሠረት ቻይና በካናዳ የካኖላ ዘይት ላይ ጥላው የነበረውን የ85% ታሪፍ እስከ መጋቢት ወር ድረስ ወደ 15% ዝቅ የምታደርግ ሲሆን፣ ካናዳ በበኩሏ በቻይና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥላው የነበረውን የ100% ታሪፍ ወደ 6.1% ዝቅ ለማድረግ ተስማምታለች።

​ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ ካናዳ ከቻይና ጋር ያላት ግንኙነት አሁን ላይ “ሊተነበይ የሚችል እና እርስ በእርስ መከባበር ላይ የተመሠረተ” እየሆነ መጥቷል። ይሁን እንጂ በሰብዓዊ መብቶች፣ በምርጫ ጣልቃ ገብነት እና በሌሎች ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ካናዳ አሁንም የራሷ የሆኑ “ቀይ መስመሮች” እንዳሏትና ከቻይና ጋር በሁሉም ነገር እንደማትስማማ አሳስበዋል።

ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በበኩላቸው፣ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ወደ ጤናማ መስመር መመለሱ ለዓለም ሰላምና መረጋጋት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል። ይህ ስምምነት የካናዳ መሪ ከ9 ዓመታት በኋላ ወደ ቻይና ያደረጉት የመጀመሪያው ጉብኝት ውጤት ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሜሪካ እየከተለችው ካለው የንግድ ፖሊሲ በተቃራኒ አገራት አዳዲስ አጋርነቶችን እየፈጠሩ መሆኑን የሚያሳይ ነው።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories