ምሥራቅ አፍሪካ በአውሮፓ የታገዱ አደገኛ ፀረ-ተባይ መድኃኒቶች መጣያ እየሆነች መሆኑ ተገለጸ

የምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና በበለጸጉት አገራት እንዳይሰሩ የታገዱና ለጤና እጅግ አደገኛ የሆኑ ፀረ-ተባይ መድኃኒቶች መጣያ እየሆነ መምጣቱን አንድ አዲስ የምርመራ ዘገባ አጋለጠ።

በኬንያ፣ በኡጋንዳ እና በታንዛኒያ የተካሄደው ይህ ጥናት እንደሚያሳየው፣ በዳበረው ዓለም በከፍተኛ ደረጃ አደገኛነታቸው የተረጋገጠ ኬሚካሎች በምሥራቅ አፍሪካ በነፃነት ለገበያ እየቀረቡ ሲሆን፣ ይህም በዜጎች ላይ ለካንሰር፣ ለዲኤንኤ መዛባት (mutation) እና ለሥነ-ተዋልዶ ችግሮች መንስኤ እየሆነ ይገኛል።

 በኡጋንዳ ውስጥ ተመዝግበው ከሚገኙ ፀረ-ተባይ መድኃኒቶች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት ምርቶቹ በተመረቱባቸው አገራት (አውሮፓና አሜሪካ) ውስጥ አገልግሎት ላይ እንዳይውሉ የታገዱ ናቸው።

 እነዚህ ኬሚካሎች ለካንሰር፣ ለዲ ኤን ኤ (DNA) መዛባት፣ ለሆርሞን መቃወስና ለሥነ-ተዋልዶ ጤና መጥፋት ምክንያት የሚሆኑ ሲሆን፣ በድንበር አቋራጭ ሕገ-ወጥ ንግድ አማካኝነት ወደ ቀጠናው በስፋት እየገቡ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

በታንዛኒያም 44 እጅግ አደገኛ ኬሚካሎችን ለማገድ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ ከኬሚካል አምራች ኩባንያዎች ጋር በተደረገ “ድርድር” እገዳው እንዲነሳ ተደርጓል። በኬንያ ደግሞ በድንበር አካባቢ በሚደረግ ሕገ-ወጥ ዝውውር (Panya routes) ምክንያት በአገር ውስጥ የታገዱ መድኃኒቶች ከጎረቤት አገራት እየገቡ በሰብሎች ላይ እየተረጩ ይገኛሉ።

በኡጋንዳ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው፣ በእነዚህ ኬሚካሎች የታከሙ ቲማቲሞችን በውሃ ማጠብ 30 በመቶ ብቻ ኬሚካሉን የሚቀንስ ሲሆን፣ ቀሪው ኬሚካል በውስጡ እንደሚቆይ ተረጋግጧል። ይህም በሕዝቡ መካከል የካንሰር ተጠቂዎች ቁጥር እንዲጨምር እያደረገ መሆኑን ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ።

የአካባቢው አርሶ አደሮች ይህንን አደገኛ ሁኔታ ለመቋቋም ወደ ተፈጥሯዊ (ኦርጋኒክ) ግብርና እየተመለሱ ይገኛሉ። በኬንያ የሚገኘው የ”ዘር አዳኞች አውታረ መረብ” ከ130,000 በላይ አርሶ አደሮች ጋር በመሆን ተፈጥሯዊ የዘር ጥበቃና ከዕፅዋት የሚዘጋጁ ፀረ-ተባይ መድኃኒቶችን እንዲጠቀሙ እያስተማረ ነው።

በተጨማሪም የ”አፍሪካ የማስተካከያና የመከላከያ እርምጃ ማዕከል” በአውሮፓና በአሜሪካ የታገዱ ኬሚካሎች በኬንያም በአስቸኳይ እንዲታገዱና በግብርና ምርቶች ላይ የጥራት ቁጥጥር እንዲጠናከር ለፓርላማ አቤቱታ አቅርቧል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories