የዓለም የገንዘብ ድርጅት አራተኛውን የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ግምገማ አጠናቀቀ

የዓለም የገንዘብ ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በኢትዮጵያ እየተተገበረ ባለው የተራዘመ የብድር አቅርቦት ፕሮግራም አራተኛውን ግምገማ ማጠናቀቁን አስታውቋል።

ቦርዱ ግምገማውን ተከትሎ ኢትዮጵያ የ261 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ብድር ወዲያውኑ እንድታገኝ የፈቀደ ሲሆን፣ ይህም አገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክፍያ ሚዛኗን እንድታስተካክልና የበጀት ፍላጎቶቿን እንድታሟላ ይረዳታል።

እስካሁን ባለው ሂደት ኢትዮጵያ ከድርጅቱ በአጠቃላይ የ2.183 ቢሊዮን ዶላር ብድር አግኝታለች።

ተቋሙ እንዳስታወቀው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙ ላይ የሚጠበቁ ግቦችን በማሳካት ረገድ ተስፋ ሰጭ ውጤቶችን እያመጣ ነዉ።

በተለይም ጠንካራ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የወጪ ንግድ መሻሻል፣ የሀገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብ መጠናከር፣ የውጭ ምንዛሬ ክምችት መጨመር እና የዋጋ ግሽበት መቀነስ በማሻሻያው የተገኙ መልካም ውጤቶች መሆናቸውን ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ገበያውን ለማረጋጋትና የገንዘብ ፖሊሲውን ለማዘመን የወሰዳቸው እርምጃዎችም አበረታች መሆናቸው ተገልጿል።

ይሁን እንጂ የሪፎርሙን ፍጥነት ጠብቆ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን ድርጅቱ አሳስቧል። የመንግሥት ወጪን በጥንቃቄ መቆጣጠር፣ የግብርና የጉምሩክ አስተዳደር ማሻሻያዎችን ማጠናከር፣ የነዳጅ ድጎማን ደረጃ በደረጃ ማንሳትን መቀጠል እና የማኅበራዊ ደኅንነት ሴፍቲኔት ድጋፎችን ማጠናከር በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸው ተጠቅሷል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ጫናዋን ለማቃለል ከአበዳሪ አገራት ጋር እያደረገችው ያለው ድርድር ውጤታማ መሆኑንና ከግል አበዳሪዎች ጋር ያለው ውይይትም መቀጠሉን ድርጅቱ በበጎ ጎኑ ገምግሞታል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories