ጋና የውጭ ኩባንያዎችን የማዕድን ስምምነቶች በመሰረዝ የወርቅ ሮያሊቲ ክፍያን በእጥፍ አሳደገች

የአፍሪካ ቀዳሚ የወርቅ አምራች የሆነችው ጋና፣ በዓለም አቀፍ ገበያ የወርቅ ዋጋ ታሪካዊ የተባለውን የ4,590 ዶላር ደረጃ መድረሱን ተከትሎ፣ አገራዊ ጥቅሟን ለማስከበር የቆዩ የማዕድን ስምምነቶችን በመሰረዝ አዲስ የታክስ መመሪያ አወጣች።

የጋና መንግሥት እንደ ኒውሞንት አንግሎ ጎልድ አሻንቲ እና ጎልድ ፊልድስ ካሉ ዓለም አቀፍ ግዙፍ ኩባንያዎች ጋር የነበሩትንና የታክስ ምጣኔው ሳይቀየር ለረጅም ዓመታት እንዲቆይ የሚያረጋግጡ የመረጋጋት ስምምነቶችን ከእንግዲህ እንደማያድስ አስታውቋል።

በተለይም ባለፈው ታኅሣሥ ወር ውሉ ያበቃው የኒውሞንት ስምምነት ያልታደሰ ሲሆን፣ የሌሎቹ ኩባንያዎች ውልም እ.ኤ.አ በ2027 ሲያበቃ በቀጥታ ወደ አዲሱ የታክስ ሥርዓት እንደሚሸጋገሩ ተገልጿል።

ይህ አዲሱ የፖሊሲ ለውጥ በአሁኑ ወቅት ከ3% እስከ 5% ያለውን የወርቅ ሮያሊቲ ክፍያ በእጥፍ በማሳደግ እስከ 12% እንዲደርስ የሚያደርግ ነው። በአዲሱ ረቂቅ ሕግ መሠረት፣ የወርቅ ዋጋ በአንድ አውንስ ከ4,500 ዶላር በላይ በሚሆንበት ጊዜ ኩባንያዎች 12% ሮያሊቲ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ።

የጋና ማዕድን ኮሚሽን ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አይዛክ ታንዶህ እንደገለጹት፣ የቆዩት ስምምነቶች መንግሥት ከሀብቱ ማግኘት የሚገባውን ገቢ እንዳያገኝ እንቅፋት ሆነው የቆዩ በመሆኑ፣ አዲሱ አሠራር በወርቅ ዋጋ መናር የሚገኘው ትርፍ ለአገሪቱ ሕዝብ እንዲተርፍ ለማድረግ ያለመ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ፣ ማዕድን አውጪ ኩባንያዎች ግብዓቶቻቸውን ከአገር ውስጥ ድርጅቶች እንዲገዙና ለጋናውያን የሥራ ዕድል ቅድሚያ እንዲሰጡ የሚያስገድዱ ጠንካራ መመሪያዎች ተካተዋል።

ይህ የጋና ውሳኔ ሌሎች የተፈጥሮ ሀብት ያላቸው አፍሪካ አገራትም (እንደ ማሊ እና ዛምቢያ) በቅርቡ ከወሰዷቸው ተመሳሳይ እርምጃዎች ጋር የሚጣጣም ሲሆን፣ አህጉሪቱ በሀብቷ ላይ ያላትን ሉዓላዊነት ለማስከበር የምታደርገው ጥረት አካል ተደርጎ ተወስዷል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories