በኢትዮጵያ የሶላር ግብርናን ለማስፋፋት የ50 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መመደብ ተዘገበ

የዓለም ባንክ እና የሮክፌለር ፋውንዴሽን ኢትዮጵያን ጨምሮ በስድስት የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ አነስተኛ ገበሬዎችን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሚያደርግ የ50 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ይፋ አደረጉ።

“Productive Use Financing Facility (PUFF)” ተብሎ የሚጠራው ይህ ፕሮግራም፣ በዋነኝነት ትኩረት የሚያደርገው ገበሬዎች በፀሐይ ኃይል (ሶላር) የሚሰሩ የግብርና መሣሪያዎችን በዝቅተኛ ዋጋ እንዲያገኙ በማድረግ ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉ መርዳት ላይ ነው።

በዚህ ፕሮጀክት አማካኝነት በሶላር የሚሰሩ የውሃ ፓምፖች፣ የቀዝቃዛ መጋዘኖች፣ ማቀዝቀዣዎች እና የእህል መፍጫ ማሽኖች ለገበሬዎች የሚሰራጩ ሲሆን፤ ይህም በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ሴራሊዮን፣ ኡጋንዳ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተግባራዊ ይሆናል።

የገንዘብ ድጋፉ ለቴክኖሎጂ አቅራቢዎች እና አከፋፋዮች በእርዳታ እና በድጎማ መልክ የሚሰጥ በመሆኑ፣ ገበሬዎች መሣሪያዎቹን እጅግ በተቀነሰ ዋጋ መግዛት እንዲችሉ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።

ይህ ማስፋፊያ በተለይ በአፍሪካ እስከ 40 በመቶ የሚደርሰውን የድህረ-ምርት ብክነት ለመቀነስ ትልቅ ሚና ይጫወታል። ለምሳሌ በኬንያ የሚገኘው “SokoFresh” የተባለ ተቋም በሶላር የሚሰሩ የቀዝቃዛ መጋዘኖችን በመጠቀም፣ የገበሬዎች ምርት ለውጭ ገበያ እስኪቀርብ ድረስ እንዳይበላሽ በማድረግ ረገድ ስኬታማ ውጤት አስመዝግቧል።

ፕሮጀክቱ በሙከራ ደረጃ በቆየባቸው ያለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ብቻ 24 የሚሆኑ መሰል የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን መደገፍ ችሏል።

በተጨማሪም ፕሮጀክቱ የዓለም ባንክ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ በጋራ የቀረጹት “ሚሽን 300” የተሰኘው ታላቅ ዕቅድ አካል ነው። ይህ ዕቅድ እ.ኤ.አ. እስከ 2030 ድረስ 300 ሚሊዮን አፍሪካውያንን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት የኤሌክትሪክ አገልግሎት የማያገኙ 600 ሚሊዮን ዜጎችን ችግር ለመቅረፍ የሚደረገው ጥረት አንዱ አካል መሆኑ ተገልጿል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories