የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ግብይት ድርሻ 87.9 በመቶ ደረሰ

 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ ካከናወነው አጠቃላይ የገንዘብ እንቅስቃሴ መካከል 87.9 በመቶ የሚሆነው በዲጂታል የባንክ አማራጮች መከናወኑን አስታወቀ።

ባንኩ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ በዲጂታል የክፍያ መንገዶች ከ9 ትሪሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ማንቀሳቀስ ችሏል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስትራቴጂክ ዕቅድና ትራንስፎርሜሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ወጋየሁ ገብረማርያም እንደገለጹት ደንበኞች የዲጂታል ባንክ አገልግሎትን እንደ ባህል እየወሰዱት መምጣታቸው ለተመዘገበው ስኬት ትልቁን ድርሻ ይይዛል።

ባንኩ ባለፈው በጀት ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ በዲጂታል አማራጮች ከተንቀሳቀሰው አጠቃላይ የገንዘብ ዝውውር የ73 በመቶ ድርሻ ነበረው። በያዝነው ዓመት ግማሽ ዓመት የታየው አፈጻጸም ግን ባንኩ በሀገሪቱ የዲጂታል ፋይናንስ ዘርፍ ላይ ያለውን የበላይነት ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑ ተመላክቷል።

በተያያዘ ዜና፣ ባንኩ በዚሁ ግማሽ ዓመት ውስጥ 321 ቢሊዮን ብር ብድር ለደንበኞቹ ያቀረበ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ ከ91 በመቶ በላይ የሚሆነው (293.9 ቢሊዮን ብር) ለግሉ ዘርፍ የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

ብድሩ በዋናነት ለአምራቾች፣ ለአስመጪና ላኪዎች እንዲሁም ለተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የዋለ ሲሆን፣ 51.3 ቢሊዮን ብሩ ደግሞ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት (ሲቢኢ ኑር) ለሚጠቀሙ ደንበኞች የቀረበ መሆኑ ተጠቁሟል።@SECO

Related

በግሎባል ባንክ የ18 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ግዢ እና የአመራር ውዝግብ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስነሳ

በቅርቡ ከፍተኛ የአመራርና የመልካም አስተዳደር ውዝግብ ውስጥ የገባው ግሎባል...

ዘመን ባንክ የኢንተርፕራይዞች የአሰራር ክፍተት ለመሙላት እየሰራ ነው

የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበት ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል የዘመን ባንክ...

አንበሳ ባንከ በተፈጠረበት ጫና ብሄራዊ ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ

አዲሱ ቦርድ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለም ተብሏል ባለፈው አመት የተደረገውን...

ዘምዘም ባንክ የሀብት መጠኑ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ

ባንኩ 1.56 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ዘምዘም ባንክ...

የዳሽን ባንከ አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ወረቀት አልባ መግባቱን ባንኩ አስታወቀ

የሱፐር አፕ እለታዊ የገንዘብ ዝውውር 3.7 ቢሊየን ብር ተሻግሯል በአብዱልሰመድ...

Popular Categories