1.75 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ዘመናዊ የማቀዝቀዣ መጋዘንና ሁለገብ ሕንፃ ተመረቀ

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ያስገነባውና ለግብርና ምርቶች እንዲሁም ለእንስሳት ተዋጽኦ ክምችትና ስርጭት የሚውል ግዙፍ የማቀዝቀዣ መጋዘንና ሁለገብ ሕንፃ በዛሬው ዕለት ከንቲባ አዳነች አቤቤና በከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተመርቋል።

በ11,437 ካሬ ሜትር ምድረ ግቢ ላይ ያረፈውና 1.75 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ይህ ግዙፍ መሰረተ ልማት፣ በአንድ ጊዜ ከ20 ሺህ ኩንታል በላይ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የእንስሳት ተዋጽኦን የማቀዝቀዝ እና 10 ሺህ ኩንታል የማደራጀት አቅም ያለው ዘመናዊ መጋዘን እንዲሁም ባለ 10 ወለል ሁለገብ ሕንፃን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ የንግድ መሰረተ ልማት የሀገሪቱን የንግድ ሥነ-ምህዳር ለማዘመንና በዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ውስጥ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚከናወኑ መጠነ ሰፊ ሥራዎች አካል ሲሆን፣ የታዩ ክፍተቶችን በአጭር ጊዜ ለማረም የሚያስችል የአሰራር ማሻሻያና ያላሰለሰ የአመራር ክትትል ተደርጎበት የተጠናቀቀ መሆኑ ተጠቁሟል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories