የዘመን ባንክ አጠቃላይ ሀብቱ ከ100 ቢሊዮን ብር ማለፉን አስታወቀ

የተከፈለ ካፒታሉም14 ቢሊዮን ብር ደርሷል

ዘመን ባንክ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ መንፈቅ አጠቃላይ ሀብት 106 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታውቋል፡፡

የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ ደግሞ 80 ቢሊዮን ብር መድረሱ ባንኩ ለቅዳሜ ገበያ በላከው መግለጫ ገልጿል፡፡

ይህም ባንኩ የተረጋጋ ዕድገትና ጠንካራ የደንበኞች እመኔታ እንዳለው የሚያሳይ መሆኑን አቶ ደረጀ ዘበነ የዘመን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስታወቁ።

ባንኩ በዚሁ ጊዜ ውስጥ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡንና የባንኩን የተከፈለ ካፒታል 14 ቢሊዮን ብር ማድረሱን አቶ ደረጀ ገልፀዋል፡፡

የተመዘገባው ውጤት ካለፈው ዓመት ከነበረ የሥራ አፈፃፀም ሲወዳደር የዘንድሮው የላቀና ስኬታማ የሥራ ጊዜ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ እንዬ ቢምር  በሁለተኛው አጋማሽ ዓመትም የተሻለ ውጤት ለማግኘት ጠንክሮ መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የባንኩ እድገት የሚገለፀው ለኢኮኖሚው በሚያደርገው አስተዋፅኦ መሆኑን የገለፁት ዋና ሥራ አስፈፃሚው የባንኩ እድገት የደንበኞቻችን እድገት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ባንኩ በገበያው ውስጥ የብድር አቅርቦት እንዲጨምር ቁጠባን በማሰባሰብ፤ ኢንቨስትመንት እንዲያድግ በማገዝ እንዲሁም የውጪ ምንዛሬ ግኝት ከፍ እንዲልና ሀገሪቱ ከዚህ ተጠቃሚ እንድትሆን አስተዋፅኦ እንዳለው አስታውቀዋል።

ዘመን ባንክ በ2001 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን አላማውም በሀገራችን በተለየና ዘመናዊ በሆነ አሠራር አዳዲስና የተመረጡ የባንክ ምርቶችንና አገልግሎቶችን በማቅረብ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ባንኩ ባለፉት 17 አመታት ሥራ አድማሱን በማስፋትና በአንድ ቅርንጫፍ ከሚሰጥ ኮርፖሬት እገልግሎት በመነሳት ቅርንጫፎቹን በማብዛት ለሁሉም ደንበኞቹ ይበልጥ ተደራሽ ሆኗል፡፡@SECO

Related

በግሎባል ባንክ የ18 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ግዢ እና የአመራር ውዝግብ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስነሳ

በቅርቡ ከፍተኛ የአመራርና የመልካም አስተዳደር ውዝግብ ውስጥ የገባው ግሎባል...

ዘመን ባንክ የኢንተርፕራይዞች የአሰራር ክፍተት ለመሙላት እየሰራ ነው

የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበት ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል የዘመን ባንክ...

አንበሳ ባንከ በተፈጠረበት ጫና ብሄራዊ ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ

አዲሱ ቦርድ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለም ተብሏል ባለፈው አመት የተደረገውን...

ዘምዘም ባንክ የሀብት መጠኑ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ

ባንኩ 1.56 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ዘምዘም ባንክ...

የዳሽን ባንከ አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ወረቀት አልባ መግባቱን ባንኩ አስታወቀ

የሱፐር አፕ እለታዊ የገንዘብ ዝውውር 3.7 ቢሊየን ብር ተሻግሯል በአብዱልሰመድ...

Popular Categories