የግብይት አውታሩ በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ላለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና ለፋይናንስ ዘርፍ ዘመናዊነት ወሳኝ ምዕራፍ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
በባንኮች መካከል በሚደረገው የውጭ ምንዛሪ ገበያ ውስጥ ግልጽነትን፣ ትክክለኛ ዋጋን የማወቅ ሂደትንና የገበያ ሥርዓትን እንደሚያጠናክር ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በባንኮች መካከል የሚካሄድ የውጭ ምንዛሪ አውቶማቲክ የንግድ አውታር (Platform) ለተሳታፊ ሁሉ ግልጽ፣ ፈጣንና በመመሪያ የተመራ የገበያ አካባቢ ይፈጥራል ብለዋል።
መድረኩ የገበያ ዲሲፕሊንን ለማጠንከር፣ የዋጋ ሂደትን ለማሻሻልና የፋይናንስ ገበያ ሪፎርምን ለመደገፍ ትልቅ ግብዓት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡@SECO


