የኢትዮ ቴሌኮም  ባለፉት ስድስት ወራት  85 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

ካምፓኒው 2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ስራ አፈፃፀሙን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደገለጹት ኩባንያው ባለፉት ስድስት ወራት  በቴሌኮም መሠረተ-ልማት፣ በዲጂታል መድረኮች እና በፋይናንስ ቴክኖሎጂ ላይ የሚያደርገውን የቴሌኮምና የዲጂታል መሰረተ ልማት ማስፋፊያ የሞባይል ኔትወርክ ማስፋፊያ ስራዎች  አከናውኗል።

በዚህም ካምፓኒው  በግማሽ አመቱ  278 አዳዲስ የሞባይል ጣቢያዎችን ገንብቶ ወደ ሥራ ያስገባ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 130 ያህሉ  በገጠር አካባቢዎች እንደሆነ ተናግረዋል።

 በተከናወኑ የኔትወርክ ማስፋፊያ ስራዎች 133 አዳዲስ ከተሞች የ4G አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን የቻሉ ሲሆን ይህም አጠቃላይ የ4G ተጠቃሚ ከተሞችን ቁጥር ወደ 1,069  አድርሷል።

ካምፓኒው ባከናወነው ሰፊ ስራ ባለፉት ስድስት ወራት  85.02 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቀዋል።

ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ37% ጭማሪን እንዳለው ጠቁመዋል።

ለገቢው ዕድገት የደንበኞች ቁጥር መጨመር፣ በደንበኛ አጠቃቀም እድገት የትራፊክ መጨመር፣ የ4ጂ ኔትወርክ አቅም መጨመር እና መሻሻል፣ የመሰረት ልማት መስፋፋት፣ የአዳዲስ የምርት እና አገልግሎቶች አቅርቦት፣ ከአጋሮች ጋር ያለው የትብብር እድገት፣ እና የውስጥ አሰራር መዳበር፣ የሰራተኞች እና የአመራር የአቅም መጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል የውጭ ምንዛሪ እጥረት የዲቫይስ እና የኢንተርፕራይዝ ሶሉሽን የገቢ አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳሰሩን ተንናግረዋል።

ካምፓኒው በስድስት ወራቱ የውጭ ምንዛሪ ለማመንጨት ባከናወነው ስራ  88.19 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር  ማግኘቱን ተናግረዋል።

ከተገኘው ገቢ ውስጥ 69 ሚሊዮን ዶላር ከአለም አቀፍ አገልግሎት እንዲሁም 3.16 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ ከመሰረተ ልማት ማጋራት ኪራይ የተገኘ እንደሆነ ተገልጿል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories