በኢንቨስትመንት ማማከር አገልግሎት ዘርፉ ላይ የብቃት መስፈርትና የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ሥርዓት ለመዘርጋት ዝግጅት ማጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ

የአውሮፓ ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ሲገቡ የሚገጥሟቸውን የመረጃ አቅርቦት ችግሮች ይቀርፋል የተባለ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት የልህቀት ማዕከል  ተከፈተ

በኢትዮጵያ የአውሮፓ የንግድ ምክር ቤት አዲስ ቢሮ እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት የልህቀት ማዕከል  ምቃት ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር  ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር ) የቢሮ እና  የልህቀት ማዕከከሉ  መከፈት የአውሮፓ ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ሲገቡ የሚገጥሟቸውን የመረጃ አቅርቦት ችግሮች በመቅረፍ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።

ጥራት ያለው የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ተዓማኒነት ያለው የማማከር አገልግሎት አስፈላጊ መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነሩ ቀደም ሲል ብቃታቸው ባልተረጋገጡ አካላት የሚሰጡ የተሳሳቱ መረጃዎች ባለሀብቶችን ለስህተት ሲዳርጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይም ችግሩን ለመቅረፍ ኮሚሽኑ በኢንቨስትመንት ማማከር አገልግሎት ዘርፉ ላይ ጥብቅ የብቃት መስፈርትና የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ሥርዓት ለመዘርጋት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቀዋል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories