ሞሮኮ የመጀመሪያውን የፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ  ተርሚናል የሚያስተናግደውን የ5.6 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ ወደብ ልታስመርቅ ነው

ሞሮኮ በሜዲትራኒያን ባህር ላይ የሚገኘውን ሁለተኛውን ጥልቅ የባህር ወደብ “ናዶር ዌስት ሜድ” በዚህ ዓመት አራተኛ ሩብ ዓመት ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ዝግጅቷን አጠናቃለች።

በ5.6 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካና በሜዲትራኒያን ቀዳሚ የሆነውን “ታንጀር ሜድ” ወደብ ስኬት ለመድገም ያለመ ሲሆን፣ በዓመት 5 ሚሊዮን ኮንቴይነሮችን የማስተናገድ የመጀመርያ አቅም ይኖረዋል።

እንደ ንጉሥ መሐመድ ስድስተኛ ገለጻ፣ ወደፊት ፍላጎቱ ሲጨምር የወደቡን አቅም እስከ 12 ሚሊዮን ኮንቴይነሮች ለማሳደግ ታቅዷል። ወደቡ 5.4 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ማዕበል መከላከያ፣ 4 ኪሎ ሜትር የክዋይ (quay) ርዝመትና አራት የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ያካተተ ዘመናዊ የንግድ መተላለፊያ ይሆናል።

የዚህ ፕሮጀክት ዋነኛውና ልዩ መለያው የሀገሪቱን የመጀመሪያ የፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ (LNG) ተርሚናል የሚያስተናግድ መሆኑ ነው። በዓመት 5 ቢሊዮን ኩቢክ ሜትር ጋዝ የማስተናገድ አቅም ያለው ይህ ተርሚናል፣ የሞሮኮን የኢነርጂ ዋስትና ከማጠናከሩ ባለፈ ለኢንዱስትሪ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሎ ይጠበቃል።

 ከወደቡ ጎን ለጎን ለኢንዱስትሪና ለሎጂስቲክስ አገልግሎት የሚውል 700 ሄክታር መሬት የተከለለ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስ 20 ቢሊዮን ዲርሃም የሚጠጋ የግል ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሉ ተገልጿል። ናዶር ዌስት ሜድ ሙሉ በሙሉ ሥራ ሲጀምር ሞሮኮ በአህጉራዊና በዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች ላይ ያላትን ተፅዕኖ በማሳደግ ቀጣናዊ የንግድና የኢነርጂ ማዕከልነቷን እንደሚያረጋግጥላት ይታመናል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories