የአውሮፓ ህብረት ከሩሲያ ጋዝ ጋር በተያያዘ ለአሜሪካና ለኳታር ልዩ የፍተሻ ነፃነት ሊሰጥ ነው

የአውሮፓ ህብረት ከሩሲያ የሚገባውን ጋዝ ሙሉ በሙሉ ለማገድ ባወጣው አዲስ መመሪያ፣ እንደ አሜሪካ እና ኳታር ካሉ ቁልፍ አቅራቢዎች የሚመጣ ጋዝ ከከባድ ፍተሻ ነፃ እንዲሆን የሚያስችል ረቂቅ ሰነድ ይፋ አደረገ።

ህብረቱ እ.ኤ.አ. በ2027 መጨረሻ ላይ ከሩሲያ የሚመጣን ማንኛውንም የጋዝ ምርት ለማቆም በህግ የተደገፈ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። ይህንን እገዳ በተግባር ለማዋልም፣ ከሩሲያ ውጭ ካሉ ሀገራት የሚመጡ የጋዝ ምርቶች ወደ አውሮፓ ከመድረሳቸው አምስት ቀናት በፊት የት ሀገር እንደተመረቱ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ለጉምሩክ ባለስልጣናት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ሆኖም በሮይተርስ የታየው የአውሮፓ ኮሚሽን ረቂቅ ሰነድ እንደሚያሳየው፣ ይህ ጥብቅ የፍተሻ መስፈርት ለተወሰኑ ሀገራት ተፈጻሚ አይሆንም። የፍተሻ ነፃነት የተሰጣቸው ሀገራት አሜሪካ፣ ኖርዌይ፣ ኳታር፣ ብሪታንያ፣ አልጄሪያ እና ናይጄሪያ ናቸው።

እነዚህ ሀገራት ከፍተሻ ነፃ የተደረጉት፣ የሩሲያ ጋዝ ወደ ምርታቸው የመቀላቀል እድሉ ዝቅተኛ በመሆኑ እና የራሳቸው ጠንካራ የኃይል አቅርቦት መሰረተ ልማት ያላቸው በመሆኑ ነው።

በ2025 በነበረው መረጃ መሠረት፣ ኖርዌይ 89 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ጋዝ በማቅረብ ለአውሮፓ ህብረት ቀዳሚዋ የጋዝ አቅራቢ ስትሆን፣ አሜሪካ በ81 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች። በአንጻሩ የቀድሞዋ ግዙፍ አቅራቢ ሩሲያ ለአውሮፓ የምታቀርበው መጠን ወደ 37 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ዝቅ ብሏል።

ይህ አዲስ መመሪያ በቅርብ ቀናት ውስጥ ይፋ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የአውሮፓ ህብረት በኃይል አቅርቦት ረገድ በሩሲያ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ የጀመረውን ጥረት ያጠናክረዋል ተብሏል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories