በ2026 የዓለም የኃይል ዘርፍ የታሪክ ለውጥ እንደሚገጥመው ተተነበየ

በ2026 የዓለም የኃይል ዘርፍ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያስተናግድና ለመጀመሪያ ጊዜ ታዳሽ የኃይል ምንጮች ከድንጋይ ከሰል ብልጫ በመውሰድ ዋነኛ የኃይል አቅራቢ እንደሚሆኑ የሪስታድ ኢነርጂ አዲስ ሪፖርት አመላከተ።

በሪፖርቱ መሰረት በዚህ ዓመት ሊታዩ የሚችሉ አምስት ወሳኝ ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. ታዳሽ ኃይል የድንጋይ ከሰልን ይበልጣል

ምንም እንኳን አዳዲስ የኃይል ማመንጫ ተከላዎች ፍጥነት በትንሹ ቢቀንስም፣ በ2026 ከፀሐይ፣ ከንፋስ፣ ከውኃና ከሌሎች ታዳሽ ምንጮች የሚገኘው አጠቃላይ የኃይል ምርት 11,900 TWh ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ይህም ለበርካታ አስርተ ዓመታት ቀዳሚ የነበረውን የድንጋይ ከሰል ምርት በመብለጥ ታሪካዊ ምዕራፍ ይከፍታል።

2. የታዳሽ ኃይል ማመንጫዎች ግንባታ መቀነስ

ከ2000ዎቹ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የአዳዲስ ታዳሽ ኃይል ማመንጫዎች ግንባታ መጠነኛ ቅናሽ ያሳያል። ለዚህም ዋነኛው ምክንያት በቻይና የታየው የፖሊሲ ለውጥና የገበያ መሞላት እንደሆነ ተገልጿል። በ2025 ዓለም አቀፍ አቅም 703 ጊጋ ዋት (GW) የነበረ ሲሆን፣ በ2026 ወደ 650 ጊጋ ዋት (GW) ዝቅ ይላል ተብሎ ይገመታል።

3. የባትሪ ኢነርጂ ማከማቻ መስፋፋት

ታዳሽ ኃይል አስተማማኝ እንዲሆን የባትሪ ማከማቻዎች ሚና እየጎላ መጥቷል። የባትሪ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን ተከትሎ፣ በ2026 የዓለም አቀፍ የባትሪ ማከማቻ አቅም በ50 በመቶ በማደግ 363 ጊጋ ዋት (GW) ይደርሳል ተብሏል።

4. የኒውክሌር ኃይል ዳግም መነሳት

የኃይል ዋስትናን ለማረጋገጥና ካርቦንን ለመቀነስ ሲባል የኒውክሌር ኃይል ከፍተኛ ትኩረት እያገኘ ነው። በ2026 ወደ 14 ጊጋ ዋት (GW) የሚጠጋ አዲስ የኒውክሌር ኃይል ወደ ስራ የሚገባ ሲሆን፣ ይህም ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ዓመታዊ ጭማሪ ነው። በተለይም ቻይና፣ ሕንድ እና ደቡብ ኮሪያ በዚህ ረገድ ግንባር ቀደም ናቸው።

5. የዳታ ማዕከላት የኃይል ፍላጎት

የዓለም የኃይል ፍላጎት በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ሲሆን፣ ለዚህም በዋነኝነት የዳታ ማዕከላት መስፋፋትና የትራንስፖርት ዘርፍ ወደ ኤሌክትሪክ መቀየር እንደ ምክንያት ተጠቅሰዋል።

 በ2026 ብቻ ዓለም አቀፍ የኃይል ፍላጎት 30,400 TWh ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የንግድ ዘርፉ የኃይል አጠቃቀም በ5.1 በመቶ ያድጋል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories