የገንዘብ ኖቶችን ለጌጣጌጥ መጠቀም እስከ 7 ዓመት እስራት ሊያስቀጣ እንደሚችል ተገለጠ

በኬንያ የገንዘብ ኖቶችን እንደ አበባ በመጠቅለልና በማጣበቅ ለስጦታ ማቅረብ በሕግ የሚያስቀጣ ተግባር መሆኑን የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ አስጠነቀቀ።

 ባንኩ ሰኞ ዕለት ባወጣው መግለጫ፣ በተለይ በቫለንታይን ቀን አካባቢ የሚዘወተሩት እነዚህ የገንዘብ አበባዎች ኖቶቹን በማጠፍ፣ በመለጠፍና በስቴፕለር በመምታት የገንዘቡን ጥራት እንደሚያበላሹ ገልጿል።

 ይህ ድርጊት የገንዘብ መቁጠሪያና የኤቲኤም (ATM) ማሽኖች ላይ ብልሽት ከመፍጠሩም በላይ፣ የተበላሹ ኖቶችን ለመተካት መንግሥትን ለተጨማሪ ወጪ እንደሚዳርግ ተመልክቷል።

 በዚህ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ግለሰቦችም የሀገሪቱን ገንዘብ በማርከስ ወንጀል ተከሰው እስከ ሰባት ዓመት በሚደርስ እስራት ሊቀጡ እንደሚችሉ ያሳሰበው ባንኩ፣ ሕዝቡ ገንዘብን ለስጦታነት ሲጠቀም የኖቶቹን ደኅንነት በማይነካ መልኩ እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories