ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ የማዕድን ማውጣት የምስክር ወረቀት አገኘ

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዓለም አቀፍ የሲያናይድ አጠቃቀም የጥራት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማግኘቱ ተገለፀ። ይህ ስኬት ይፋ የተደረገው የ12 ሀገራት የማዕድን ዘርፍ ተወካዮች እና የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ተዋናዮች በተገኙበትና ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የሲያናይድ ማኔጅመንት ጉባዔ ላይ ነው።

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ በጉባዔው ላይ እንደገለጹት፣ ይህ ዕውቅና ሚድሮክ ወርቅን ለማውጣት የሚጠቀምበት የሲያናይድ ሂደት የአካባቢ ጥበቃን ያገናዘበ፣ የሰራተኞችን ጤንነት የሚጠብቅ እና የህዝብን ደህንነት የሚያረጋግጥ መሆኑን በተግባር የሚያሳይ ነው።

ሚኒስትሩ አክለውም ሌሎች በዘርፉ የተሰማሩ ኩባንያዎች ይህንን አርአያነት ያለው አሰራር በመከተል ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል።

የማዕድን አመራረት ሂደት ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ በመሆኑ፣ ኩባንያው ጥብቅ የሆኑ ዓለም አቀፍ መመሪያዎችን መከተሉ ለሀገር ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ልምምድን የሚያስተምርና በዘርፉ ላይ ዋስትና የሚሰጥ መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል።

ሲያናይድ ወርቅን እስከ 97 በመቶ ድረስ የማውጣት ብቃት ያለው በመሆኑ፣ ቴክኖሎጂውን በዘመናዊና ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ መጠቀም ምርታማነትን ሳይቀንስ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ይረዳል።

የማዕድን ሚኒስቴር ሌሎች ኩባንያዎችም በተመሳሳይ የጥራት ደረጃ ሰርቲፋይድ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ሬጉሌሽን እና ክትትል እንደሚያደርግ ያስታወቀ ሲሆን፣ እንዲህ ያሉ ዓለም አቀፍ ዕውቅናዎች ኩባንያዎች ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ለሚኖራቸው አጋርነት እንዲሁም የውጭ ብድር እና ፋይናንስ ለማግኘት ትልቅ ዕድል ይፈጥራሉ።

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማዕድን ዘርፍ የአቅም  ግንባታዳ ይሬክተር  አቶ ጋዲሳ ሂርጳ እንደገለጹት  ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  በማዕድን ላይ የሚሰራ ስራ ደህንነተቱ የተጠበቀ  ለአካባቢ ትኩረት የሰጠ ለማህበረሰቡና በወርቅ ስራ ላይ ለሚገኙ ሰራተነኞችና አመራሮች ትኩረት የሰጠ ነው።

በዘርፉ ላይ የሚሰራ ስራ ውጤታማ እንዲሆን  ደህንነተቱ የተጠበቀ  መሆን እንዳለበት ነው የተናገሩት፡፡

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከብክለት የጸዳ ምርት ማምረት የሚያስችለውን መመዘኛ ለማግኘት ለሁለት አመታት በርካታ ስራዎች ሲያከናውን መቆየቱን ጠቁመው ተቋሙ በሲያናይድ ትራንስፖርት እና  ሲያናይድ አጠቃቀም  ደህንነት ባስመዘገበው ውጤት አለም አቀፍ ዕውቅና እንዳገኘ አስታውቀዋል፡፡

ጉባዔውም በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ ያለው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሲያናይድ ትራንስፖርት እና  ሲያናይድ አጠቃቀም  ደህንነት ባስመዘገበው ውጤት እንደሆነም አስረድተዋል።

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግ.ማ በ2025 ያገኘው ይህ ዓለም አቀፍ የምስክር ወረቀት፣ በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ኃላፊነት የተሞላበት አመራረት እንዲሰፍን ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በጉባዔው ላይ ተገልጿል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories