ሸበሌ ባንክ በጅቡቲ ከሚገኙ ታዋቂ የንግድ መሪዎች እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር ባካሄደው ውጤታማ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ፣ በሀገሪቱ የሚገኙ ባለሀብቶች የባንኩ ባለቤት ለመሆን ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየታቸውን አስታወቀ።
በክብር እንግድነት የተገኙት የጅቡቲ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር አቶ ኤልያስ ሙሴ፣ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ለገሰ ቱሉ እና የጅቡቲ ንግድ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ዩሱፍ ሙሴ ለባንኩ ያላቸውን ጠንካራ ድጋፍ የገለጹ ሲሆን፤ ባንኩ በቀጣናው የንግድ እና የፋይናንስ አገልግሎትን ለማሳለጥ ያለውን ሚና አድንቀዋል።
የሸበሌ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኢብራሂም ዑስማን ፋራህ እና የቦርድ አባሉ ሁሴን ቃሲም በተገኙበት በዚህ መድረክ ላይ፣ የኢትዮ-ጅቡቲ የንግድ ኮሪደር ለባንኩ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ዋነኛ የትኩረት መስመር መሆኑ ተብራርቷል።

ባንኩ ባቀረበው አጠቃላይ አፈጻጸምና የወደፊት የእድገት ተስፋ ላይ ባለሀብቶቹ ያላቸውን እርካታ የገለጹ ሲሆን፣ ይህም ለታየው ከፍተኛ የአክሲዮን ግዢ ፍላጎት ምክንያት ሆኗል።
በዚህም በመድረኩ ከተገኙ ታዋቂ የንግድ ሰዎች ከፍተኛ የአክሲዮን ግዢ የተመዘገበ ሲሆን፣ በተጨማሪም በርካታ ባንኮች እና የድርጅት ተቋማት ከፍተኛ መጠን ያለው አክሲዮን ለመግዛት ያላቸውን ፍላጎት አረጋግጠዋል።@SECO


