በኢቢቪ ዘጋቢ
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እንደገለጹት በኢንዱስትሪው ዘርፍ ከፍተኛ ስኬቶች ተመዝግቧል፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የማምረት አቅም አጠቃቀም በ2014 ከነበረበት 46 በመቶ ወደ 66.3 በመቶ ከፍ ማለቱን ነው የተናገሩት።
ተኪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ረገድም በ2014 ዓ.ም ከነበረው 2.098 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን አፈጻጸም፣ በዘንድሮው ግማሽ ዓመት ብቻ ወደ 3.4 ቢሊየን ዶላር ማደጉን ጠቁመዋል።
የሀገር ውስጥ ምርቶች የገበያ ድርሻም እጅግ አስደናቂ እድገት አሳይቷል። በ2014 ዓ.ም 30 በመቶ የነበረው የገበያ ድርሻ፣ በ2018 በጀት ዓመት አጋማሽ ወደ 45.8 በመቶ በማደግ የ53 በመቶ ብልጫ ማስመዝገብ መቻሉን አቶ መላኩ አስታውቀዋል።@SECO


