በነዳጅ የሚሰሩ ተሸከርካሪዎች ላይ የተጣለው ከፍተኛ ቀረጥ ተከትሎ በኤሌክትሪ የሚሰሩ ተሸከርካሪዎች ተፈላጊነት በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡
ኢትዮጵያ ለነዳጅ ግዢ ከፍተኛ ወጪ ከሚያወጡ አገራት መካከል የምትጠቀስ ሲሆን ይህንን ለመቀነስ ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ በነዳጅ የሚሰሩ ተሸከሪካሪዎች ላይ ከፍተኛ ቀረጥ የተጣለ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ለነዳጅ የሚደረገው ድገማ እንዲቆም ተደርጓል፡፡
ይህንን ተከትሎ በሀገሪቷ በኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ፋላጎች ጨምሯል፡፡ ኢትዮጵያ በነዳጅ በሚሰሩ ተሸከርካሪዎች ላይ የወሰደችው እርምጃ ለአካባቢ ጥበቃ ከፍተኛ አሰስተዋጽኦ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡
ከአመታት በፊት በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ቁጥር ከአንድ በመቶ በታች የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ወደ ስድስት በመቶ ከፍ ሊል ችሏል፡፡
በአፍሪካ በአማካኝ ከአንድ ሺህ ሰዎች 73 ያህሉ ተሸከራካሪ ሲኖራቸው በኢትዮጵያ ይህ ቁጥር ወደ 13 ዝቅ ያለ ነው፡፡@SECO

