ከየካቲት 1 ጀምሮ በዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ላይ የ5 በመቶ የክፍያ ጭማሪ ተግባራዊ መሆን መጀመሩ ተነገረ

በኢቢቪ ዘጋቢ

ከየካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በሚፈጸሙ ማንኛውም የባንክ ግብይቶች ላይ አዲስ የአገልግሎት ክፍያ ስሌት ተግባራዊ እንዲሆን መወሰኑን ተከትሎ፣ በዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ላይ የ5 በመቶ የክፍያ ጭማሪ መደረጉ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለሁሉም ባንኮች ባስተላለፈው ጥብቅ ማሳሰቢያ መሠረት፣ በደንብ ቁጥር 576/2018 ዓ.ም. በተቀመጠው ስሌት መሠረት ክፍያዎችን በመሰብሰብ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለተከፈተው “የኢትዮጵያ አደጋ ስጋትና ምላሽ ፈንድ” ገቢ እንዲያደርጉ ታዘዋል።

በዚህም መሠረት የዲጂታል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ከሚከፍሉት መደበኛ የአገልግሎት ክፍያ ላይ የ5% ተጨማሪ ክፍያ የሚሰበሰብ ሲሆን፣ ባንኮች ከሚሰጡት መደበኛ ብድር ላይም የ1% የፈንድ ክፍያ ተጨምሮ እንደሚሰበሰብ ታውቋል።

በተያያዘም ይህ የገቢ አሰባሰብ መመሪያ ሌሎች ዘርፎችንም የሚጨምር ሲሆን፣ ከኢንሹራንስ ኩባንያዎች የፕሪሚየም ክፍያ ላይ 1%፣ ከአገር ውስጥ አየር በረራ የቲኬት ሽያጭ ላይ 100 ብር፣ ከቴሌኮም ድምፅና ዳታ አገልግሎት 5%፣ እንዲሁም ከነዳጅ ሽያጭ በእያንዳንዱ ሊትር ላይ 1 ብር ለፈንዱ ገቢ ይደረጋል።

ይህ አዲስ አሰራር የአገሪቱን የአደጋ ስጋት የመከላከልና ምላሽ የመስጠት አቅም ለማጠናከር ታስቦ የተዘረጋ ሲሆን፣ የተሰበሰበው ገንዘብ በየወሩ ለፈንዱ ገቢ እንዲደረግ መመሪያ ተሰጥቷል።@SECO

Related

በግሎባል ባንክ የ18 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ግዢ እና የአመራር ውዝግብ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስነሳ

በቅርቡ ከፍተኛ የአመራርና የመልካም አስተዳደር ውዝግብ ውስጥ የገባው ግሎባል...

ዘመን ባንክ የኢንተርፕራይዞች የአሰራር ክፍተት ለመሙላት እየሰራ ነው

የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበት ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል የዘመን ባንክ...

አንበሳ ባንከ በተፈጠረበት ጫና ብሄራዊ ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ

አዲሱ ቦርድ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለም ተብሏል ባለፈው አመት የተደረገውን...

ዘምዘም ባንክ የሀብት መጠኑ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ

ባንኩ 1.56 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ዘምዘም ባንክ...

የዳሽን ባንከ አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ወረቀት አልባ መግባቱን ባንኩ አስታወቀ

የሱፐር አፕ እለታዊ የገንዘብ ዝውውር 3.7 ቢሊየን ብር ተሻግሯል በአብዱልሰመድ...

Popular Categories