ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥምረት በኢራን ላይ የተሰነዘረውን ከፍተኛ ወታደራዊ ጥቃት ተከትሎ፣ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ የዋጋ መናር ተመዝግቧል።
የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በዛሬው የንግድ ውሎ በ13 በመቶ በመጨመር በአንድ በርሜል 82 ዶላር ደርሷል። ይህም ባለፉት 14 ወራት የታየ ከፍተኛው የዋጋ መጠን መሆኑ ተገልጿል።
ለዋጋው መናር ዋነኛው ምክንያት ለዓለም የነዳጅ ንግድ እጅግ ወሳኝ የሆነው የሆርሙዝ ሰርጥ እንቅስቃሴ መገታቱ ነው።
ኢራን በጥቃቱ ሳቢያ በሰርጡ በኩል የሚያልፉ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ መስጠቷን ተከትሎ፣ በአሁኑ ወቅት ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥምረት በኢራን ላይ የተሰነዘረውን ከፍተኛ ወታደራዊ ጥቃት ተከትሎ፣ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ የዋጋ መናር ተመዝግቧል።
የዓለም አቀፉ የባህር ላይ ትራንስፖርት ድርጅት መርከቦች አካባቢውን እንዲያስወግዱ ያሳሰበ ሲሆን፣ እንደ Maersk ያሉ ግዙፍ የጭነት ኩባንያዎች በሆርሙዝ እና በሱዌዝ ቦይ በኩል የሚያደርጉትን ጉዞ ለደህንነት ሲሉ ማቋረጣቸውን በይፋ አስታውቀዋል።@SECO

