አንዳንድ ነጥቦች ስለ ሆርሙዝ ሰርጥ‼️
በእስራኤልና አሜሪካ በኢራን ላይ በከፈቱት ጦርነት የመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ተናግቷል፡፡ ይህንን ተከትሎ ኢራን ዘወትር እንደምትዝተው የሆርሙዝ ሰርጥን ትዘጋለች ተብሎ ተፈርቷል፡፡
ለመሆኑ የሆርሙዝ ሰርጥ አኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ምን ይመስላል የሚለውን በጥቂቱ እንመልከት፡፡
✳️ የሆርሙዝ ሰርጥ በዓለም ላይ ከሚገኙ ከፍተኛ አስፈላጊ በባህር ነዳጅ ማስተላለፊያ መስመሮች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳል‼️
✳️ በኢራን እና በኦማን መካከል የሚገኘው ይገኛል የሆርሙዝ ሰርጥ የፐርሺያ ባህርን ከኦማን ባህር ጋር ያገናኛል‼️
✳️ በየቀኑ የዓለም አጠቃላይ የነዳጅ ፍጆታ 20–25% በዚህ መንገድ ይተላለፋል‼️
✳️ የሆርሙዝ ሰርጥ ከኢራን፣ ከኢራቅ፣ከኩዌት፣ከኳታር እና ከተባበሩት አረብ ኤምሬት ወደ ውጭ የሚላክ ዘይት የሚተላለፍበት ሰርጥ ነው‼️
✳️ በዓለም ላይ በባህር ከሚጓጓዝ ነዳጅ 25 በመቶው በሆርሙዝ ሰርጥ የሚልፍ ሲሆን ከዚህም ውስጥ አብዛኛው መዳረሻቸው ቻይና፣ ሕንድ፣ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ነው‼️
✳️ የሆርሙዝ ሰርጥ የቦታው ስፋቱ 21 ማይል (34 ኪ.ሜ) ብቻ ነው። ነገር ግን የመርከቦች መስመሮች በእያንዳንዱ አቅጣጫ 3 ኪ.ሜ ብቻ ናቸው። ይህም መንገዱን በቀላሉ ሊዘጋ ወይም መተላለፊያ ለመከልከል እንዲቻል ያደርገዋል‼️
✳️ የሆርሙዝ ሰርጥን ብዙ ጊዜ ኢራን መተላለፊያውን እዘጋዋለሁ በማለት የተቀረውን አለም የምታስፈራራበት አንዱ መሳሪያዋ ሆኖ ትገለገልበታለች‼️
✳️ የሆርሙዝ ሰርጥ ማንኛውም እንቅፋት ወይም መዘጋት የዓለም የነዳጅ ዋጋ በፍጥነት እንዲጨምር ያደርጋል‼️@SECO


