በመካከለኛው ምስራቅ በቀጠለው ከፍተኛ ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ የተፈጠረውን የጸጥታ ሥጋት ለመቆጣጠር፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የሀገሪቱ የንግድ የገበያ ማዕከላት ለሁለት ተከታታይ ቀናት ዝግ ሆነው እንዲቆዩ መወሰኑን አስታወቀ።
የሀገሪቱ የፋይናንስ ተቆጣጣሪ ተቋም ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ የአቡ ዳቢ ሴኩሪቲስ ኤክስቼንጅ እና የዱባይ ፋይናንሺያል ማርኬት ዛሬ ሰኞ የካቲት 23 እና ነገ ማክሰኞ የካቲት 24 ዝግ ሆነው ይቆያሉ።
ባለሥልጣኑ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው የሀገሪቱን የፋይናንስ ሥርዓት ደህንነት ለመጠበቅ እና በቀጠናው እየታዩ ያሉ ድንገተኛ ክስተቶች በገበያው ላይ ሊያመጡ የሚችሉትን ያልተገባ መዋዠቅ ለመከላከል ካለው ኃላፊነት በመነሳት መሆኑን ገልጿል።
ይህ ያልተጠበቀ የገበያ መዘጋት እርምጃ የተወሰደው በኢራን፣ በአሜሪካ እና በእስራኤል መካከል እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ ግጭት ወደ አደገኛ ምዕራፍ መሸጋገሩን ተከትሎ ነው።
በተለይም በሆርሙዝ ወሽመጥ አካባቢ የተሰነዘሩ ጥቃቶች እና የንግድ መርከቦች መታገዳቸው በባህረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤት (GCC) አባል ሀገራት ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል።@SECO


