ከ2.6 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የኢንዘቨስትመንት ዕድል ይፈጥራል የተባለ የኢንቨስትመንት ፎረም ሊካሄድ ነው

በዓለምሰገድ እስጢፋኖስ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን(ዶ/ር) እንዳስታወቁት በ4ኛው ኢንቨስትመንት  ፎረም ላይ የኢትዮጵያን ያላትን ምቹ የኢንቨስትመንት ምህዳር በስፋት የሚያሳይ እና የማከሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የፈጠረውን ምቹ የኢንቨስትመንት እድል በስፋት ይተዋወቃሉ ።

 ባለፈው  አመት የተካሄደው 3ተኛው በኢትዮጱያ ኢንቨስት ያድርጉ አለም አቀፍ ፎረም በማዕድንና በሶላር ምርት የተሳተፉ 5 ድርጅቶች በ1.6 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር መፈራረማቸውን ጠቁመው  ድርጅቶቹ ወደ ስራ ገብተው ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ እያቀረቡ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በ4ተኛው በኢትዮጱያ ኢንቨስት ያድርጉ አለም አቀፍ ፎረምም ከ2.6ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚያወጡ ስምምነቶችን ለመፈራረም መታቀዱን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

በፎረሙ ላይ በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና፣ በማዕድን፣ በታዳሽ ኃይል፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና በቱሪዝም ዘርፎች ላይ ያተኮሩ የጎንዮሽ ውይይቶችና የንግድ ለንግድ ትስስሮች ይከናወናሉ።

ፎረሙ “ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ዝግጁ ናት በሚል መሪ ቃል በስካይ ላይት ሆቴል መጋቢት 17 እና 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄድ ሲሆን ከ800 በላይ ዓለም አቀፍ ባለሀብቶች፣ የንግድ መሪዎች ፖሊሲ አውጪዎች እና የልማት አጋሮች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories