ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል በኢራንላይ የከፈቱትን ጥቃትና ኢራንም በበኩሏ እየወሰደች ያለችውን የአጸፋ ጥቃት ተከትሎ የቀጠለው ግጭት፣የአፍሪካን ኢኮኖሚ በእጅጉ ሊጎዳ እንደሚችል የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ክቡር ገና ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በዚህ ጦርነት ምክንያት ብዙ የንግድ መስመሮች ይቃወሳሉ።
አፍሪካ በመካከለኛው ምስራቅ የቀጠለው ጦርነት ተሳታፊ ባትኾንም የገፈቱ ቀማሽ መኾኗ ግን አልቀረም። ቅደሜ የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ/ም ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን ጥቃትና ኢራንም በበኩሏ እየወሰደች ያለችውን የአጸፋ ጥቃት ተከትሎ አፍሪካም ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልኾነ ተጽዕኖ እንዳያጋጥማት ተሰግቷል ።
አቶ ክቡር ገና እንደገለፁት በተለይ የአህጉሪቱ ኢኮኖሚያ ከተጽዕኖ አያመልጥም።
“ጦርነቱ እስከ መቼ ድረሰ ይቀጥላል የሚለው ባይታወቅም፣ከነዳጅ ወጋ ጋር የተያያዘ ከፍተኛ ችግር ያመጣል የሚል ግምት አለ።በርግጥ አንዳንድ የነዳጅ አውጭ አገራት የሚጠቀሙም ቢኾኑ፣በአብዛኛው ደግሞ ነዳጅ አምራች ባለመኾናቸው፣በዛ በኩል ኢኮኖሚያቸው ሊጎዳ ይችላል” በማለት አስረድተዋል።
የዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤል ጥቃትም ሆነ ኢራን በባህረ ሰላጤው አገራት ውስጥ በሚገኙ የዋሽንግተን ወታደራዊ ይዞታዎችና ሌሎች ኢላማዎች ላይ እየወሰደች ያለችው የአጸፋ ጥቃት፣በአገራቱ የሚገኙ አፍሪካውያን ዜጎችን ደህንነት አሳሳቢ አድርጎታል።ከዚህ ጦርነት ጋር የተያያዘ ጥቃት ያረፈበት ኢላማ ግን እስካሁን በአፍሪካ ውስጥ አልታየም።በአፍሪካ ትልቁ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሰፈር “ለሞኒዬ” በሚገኝባት ጂቡቲ ያለው የአገሪቱ ኤምባሲ ባወጣው ማሳሰቢያ ግን፣በዚያ የሚገኙ ዜጎቹ የበለጠ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክሯል። ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሰፈር የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ በጊዚያዊነት ገደብ መጣሉንም ጠቁሟል።
አቶ ክቡር እንደሚሉት፣ አፍሪካ በተፋላሚዎቹ ወገኖች የሚሰነዘረው ጥቃት ኢላማ ባትኾንም፣ከአለም የንግድ ስርዓት ጋር የተሳሰረው ኢኮኖሚዋ ግን መጎዳቱ አይቀርም።
“በዚህ ጦርነት ምክንያት ብዙ የንግድ መስመሮች ይቃወሳሉ።እንደ ኢትዮጵያ አይነት አገር እና ሌሎቹም የአፍሪካ አገራት ምርታቸውን ወደ ውጭ የሚልኩት ወይም ደግሞ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቡት በዋጋም ኾነ በተለያየ ሁኔታ መጎዳታቸው አይቀርም” በማለት አብራርተዋል።
የዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤል ጥቃትም ሆነ ኢራን በባህረ ሰላጤው አገራት ውስጥ በሚገኙ የዋሽንግተን ወታደራዊ ይዞታዎችና ሌሎች ኢላማዎች ላይ እየወሰደች ያለችው የአጸፋ ጥቃት፣በአገራቱ የሚገኙ አፍሪካውያን ዜጎችን ደህንነት አሳሳቢ አድርጎታል።የዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤል ጥቃትም ሆነ ኢራን በባህረ ሰላጤው አገራት ውስጥ በሚገኙ የዋሽንግተን ወታደራዊ ይዞታዎችና ሌሎች ኢላማዎች ላይ እየወሰደች ያለችው የአጸፋ ጥቃት፣በአገራቱ የሚገኙ አፍሪካውያን ዜጎችን ደህንነት አሳሳቢ አድርጎታል።
የዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤል ጥቃትም ሆነ ኢራን በባህረ ሰላጤው አገራት ውስጥ በሚገኙ የዋሽንግተን ወታደራዊ ይዞታዎችና ሌሎች ኢላማዎች ላይ እየወሰደች ያለችው የአጸፋ ጥቃት፣በአገራቱ የሚገኙ አፍሪካውያን ዜጎችን ደህንነት አሳሳቢ አድርጎታል።
አፍሪካ በመግለጫና በሌሎችም መንገዶች የምታንፀባርቀው አቋም በበቂ ሁኔታ ይሰማል የሚል እምነት እንደሌላቸው አቶ ክቡር ገና አመልክተዋል።
“በመሠረቱ አፍሪካ በጂኦ ፖለቲካም፣በኢኮኖሚም በውትድርናም ከሌሎች አለማት ያነሰ ወይም የደከመ ቦታ ላይ ስላለች፣ይሄንን ሁኔታ በድምፅ ወይ በጽሑፍ ከመቃወም ውጭ ሌላ ለማድረግ የምትችለውና የምታስበውም ነገር ያለ አይመስለኝም” ብለዋል።
ለአፍሪካ አገራት የሚበጀውም የበለጠ በኢኮኖሚ መተሳሰር እንደኾነ የኢኮኖሚ ባለሙያው ተናግረዋል።
“አፍሪካኖች የጀመሩትን የመሰባሰብ ሁኔተ መቀጠልና ማጠንከር ይኖርባቸዋል። በተለይ ደግሞ ከዚህ ከነጻ ንግድ ስምምነት በኋላ ብዙም ለውጥ ባይታይም፣ ያንን የበለጠ ለማጠናከር የሚችሉበት አዲስ አጋጣሚ አለ ብዬ ነው የምገምተው።መገንዘብ ያለብን ነገር ቢኖር፣አንድ ላይ ጥንካሬያችንን ማምጣት ካልቻልን የሌሎች ጠንካራ አገሮች መጫወቻ ልንኾን እንደምንችል ነው,” በማለት ገልፀዋል።@SECO


