ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለሁለት አስርት ዓመታት ስታካሂድ የቆየችውን ድርድር ለማጠናቀቅ ወሳኝ የተባለውን 7ኛ ዙር የስራ ቡድን ስብሰባ በመጪው ሚያዝያ 14 እና 15 ቀን 2018 ዓ.ም በጄኔቫ እንደምታካሂድ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
የአባልነት ሂደቱ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም፣ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ብቻ በአዲስ መልክ በተደራጀው ብሔራዊ ድርድርና ቴክኒክ ኮሚቴ አማካኝነት ሦስት የስራ ቡድን ድርድሮች መካሄዳቸው ተገልጿል።
ለሚያዝያው ድርድር የተደረጉ ዋና ዋና ዝግጅቶች
* ከአባላት ለቀረቡ ከ200 በላይ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷል።
* ከስምንት በላይ የድርድር ሰነዶች ተከልሰው ለአባል ሀገራት እንዲደርሱ ተደርጓል።
* በፋይናንስ ሴክተር እና በውጭ ምንዛሬ ስርዓት ላይ የተደረጉ የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በዝርዝር ተካተዋል።
ኢትዮጵያ በድርድር ሰነዶቿ ውስጥ የንግድ ስራ ምቹነትን ለመፍጠር እና የኢንቨስትመንት ከባቢን ለማሻሻል ያከናወናቸውን ተግባራት ግልጽ አድርጋለች።
የሀገሪቱን የአባልነት ሂደት በዚሁ በፈረንጆቹ የ2026 ዓመት ለማጠናቀቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን አረጋግጧል።@SECO


