የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት እና የኢንሹራንስ ዋስትና መቋረጥ በዓለም የንግድ መስመር ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቀነ

በኢራን፣ በእስራኤል እና በአሜሪካ መካከል ያለው ወታደራዊ ፍጥጫ ተባብሶ መቀጠሉን ተከትሎ፣ የኢራን አብዮታዊ ዘበኛ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው የሆርሙዝ ሰርጥ “ተዘግቷል” ሲል ባወጀው መነሻ ዓለም አቀፍ የባህር ላይ ኢንሹራንስ ሰጪዎች የጦርነት ስጋት ዋስትና ማቋረጣቸውን አስታውቀዋል።

ይህ ውሳኔ በዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል የፈጠረ ሲሆን፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ዋስትና በመሰረዛቸው መርከቦች በባህረ ሰላጤው ውስጥ ለመንቀሳቀስ ዋስትና አጥተው እንዲገተሩ አድርጓቸዋል።

በተጨማሪም የኢንሹራንስ ክፍያ (Premiums) እስከ 300 በመቶ ሊጨምር እንደሚችል ተገምቷል። በሰርጡ መዘጋት ምክንያት በአሁኑ ወቅት ከ150 በላይ የነዳጅ እና የጭነት መርከቦች በባህር ላይ ለመቆም በመገደዳቸው የዓለም አቀፍ የሸቀጦች አቅርቦት ሰንሰለት ላይ ትልቅ ጫና አሳርፏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል የሚጓጓዘው የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት በመቋረጡ ምክንያት የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በአጭር ጊዜ ውስጥ የ13 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

በክልሉ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ቢያንስ አምስት የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ ሁለት የባህር ላይ ሰራተኞችም ህይወታቸውን አጥተዋል።

የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይህ ቀውስ በአስቸኳይ ካልተቀረፈ የዓለም አቀፍ ኢነርጂ ዋጋን የበለጠ ሊያባብሰው እና በዓለም ዙሪያ የሸቀጦች የዋጋ ንረት ሊያስከትል እንደሚችል በከፍተኛ ሁኔታ እያስጠነቀቁ ይገኛሉ።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories