በኢቢቪ ዘጋቢ
ከሳምንት በፊት ታይቶበት ከነበረው ጥንካሬ በመውረድ ብር ከሌሎች ጠንካራ ገንዘቦች አንፃር አዲስ የቅናሽ መጠን አስመዘገበ፡፡
የብር የመግዛት አቅም በትላንትናው እለት በብሄራዊ ባንክ በተደረገ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አዲስ ቅናሽ የተመዘገበበት ሆኖ ታይቷል፡፡
በእለቱ ብሄራዊ ባንክ ቀደም ሲል አሲዞት በነበረ እና በየ 15 ቀኑ በሚደረግ መርሃግብር 70 ሚሊየን ዶላር ለመሸጥ ባንኮችን ያጫረተ ቢሆንም፡፡ በጨረታው የተሳተፉ 20 ባንኮች ለመግዛት ፍላጎት ያሳዩት 177 ሚሊየን ዶላር ነበር፡፡ በዚህም ከፍተኛ የመግዣ ዋጋ ለመጀመሪያ ጊዜ 156 ብር የገባ ሲሆን በአማካኝ አንድ ዶላር በ155.94 ተሸጧል፡፡

ይህም የብር የመግዛት አቅም ለመዳከሙ አዲስ ምእራፍ ተደርጓል፡፡
ከ11 ቀናት በፊት ማእከላዊ ባንኩ ከመርሃግብር ውጭ አድርጎት በነበረ የ ግማሽ ቢሊየን ዶላር ጨረታ የብር የመግዛት አቅም ጥንካሬ አሳይቶ አንድ ዶላር በአማካኝ 153.25 ብር ተገዝቶ ነበር፡፡
ያም የጨረታ ውጤት ከቀናት በፊት (የዛሬ 15 ቀን) ተደርጎ በነበረው መደበኛ ጨረታ አንድ ዶላር ከተሸጠበት 155.12 አንፃር ጥንካሬ ያሳየበት ነበር፡፡ እንዲያም ሆኖ ትላንት ተደርጎ በነበረው መደበኛ በብሄራዊ ባንክ ጨረታ የዶላር ዋጋ ለመጀመሪያ ጊዜ 156 ብር ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ይሄም የዶላር ዋጋ ላይ የቀረበው የ155 ብር ከገባበት ያለፉት አራት ወራት ግድም አዲስ ዋጋ ሆኖ ነው የተመዘገበው፡፡©SECO


