የቡና ዋጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየቀነሰ መምጣቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ

በኢቢቪ ዘጋቢ

 የቡና አምራቾችና አቅራቢዎች በእጃቸው ያለውን የቡና ምርት በፍጥነት ወደ ገበያ ሊያቀርቡ እንደሚገባ ተጠቁሟል

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ(ዶ/ር)  ባለፉት ሁለት ወራት የቡና ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ እየቀነሰ መምጣቱን ተናግረዋል።

ቡና በተመረተበት ዓመት ለገበያ መቅረብ እንዳለበት በህግ የተቀመጠ ቢሆንም ዋጋ ይጨምራል በሚል ምርት ይዘው የተቀመጡ ላኪዎች እንዳሉ ጠቁመው ለአንድ ዓመት ያህል የዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ በዚሁ ሊቀጥል እንደሚችል ተገንዝበው በእጃቸው ያለውን ለገበያ ማቅረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ሀገራዊ የኮንትሮባንድ ንግድን የሚከላከል ግብረ ኃይል መቋቋሙን አስታውሰው በኮንትሮባንድ ለመላክ ጥረት የሚያደርጉ አካላት ላይ ክትትል እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

በ2017 በጀት ዓመት 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር በላይ ከቡና ወጪ ንግድ ገቢ መገኘቱን ጠቁመው  በዘንድሮ በጀት ዓመትም 3 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት  እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከ2ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ቡናን ለዓለም አቀፍ ገበያ ማቅረብ እንዲችሉ የላኪነት ፈቃድ ማግኘታቸውን ጠቁመው፤ 500 ያህሉ ቀጥታ እያቀረቡ እንደሚገኙ ተናግረዋል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories