በቻይና የ83 ቢሊዮን ዶላር ግምት ያለው እጅግ ግዙፍ የወርቅ ክምችት ተገኘ

በቻይና ሁናን ግዛት በሚገኘው ዋንጉ በተባለ የከርሰ ምድር ክፍል፣ በገንዘብ ሲተመን በግምት 82.8 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር (600 ቢሊዮን ዩዋን) የሚያወጣ እጅግ ከፍተኛ መጠን ያለውና ጥራቱ የላቀ የወርቅ ክምችት መገኘቱን የጂኦሎጂ ተመራማሪዎች አስታውቀዋል።

እስካሁን በተደረገው ጥናት 300.2 ሜትሪክ ቶን ወርቅ መኖሩ የተረጋገጠ ቢሆንም፣ ተመራማሪዎች በኮምፒውተር የታገዘ የ3D ጂኦሎጂካል ሞዴሊንግ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከ3,000 ሜትር ጥልቀት በታች ከ1,000 ሜትሪክ ቶን በላይ ተጨማሪ ወርቅ ሊኖር እንደሚችል ገምተዋል።

 ይህ ግኝት የተረጋገጠው የሁናን ግዛት የጂኦሎጂ ተቋም ተመራማሪዎች ከ2,000 ሜትር በላይ ጥልቀት ያላቸው 40 ያህል ጉድጓዶችን በመቆፈር ባደረጉት ጥልቅ ምርመራ ሲሆን፣ በአንድ ቶን አለት ውስጥ እስከ 138 ግራም የሚደርስ ወርቅ በመገኘቱ ክምችቱን በዓለም ላይ ካሉ ትልልቅ ማዕድናት ይልቅ እጅግ ከፍተኛ ጥራት ያለው ያደርገዋል።

የዓለም የወርቅ ምክር ቤት መረጃ እንደሚያመለክተው በሰው ልጅ ታሪክ እስካሁን የተቆፈረው ወርቅ በአጠቃላይ 212,491 ሜትሪክ ቶን ሲሆን፣ በአንድ ቦታ ብቻ እንዲህ ያለ ከፍተኛ መጠን ያለው ማዕድን መገኘቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የወርቅ ክምችት በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምረዋል።

ተመራማሪው ቸን ሩሊን እንደገለጹት፣ አካባቢው ከሚሊዮኖች ዓመታት በፊት ማዕድን አዘል ፈሳሾች ይፈሱበት የነበረ ጥንታዊ የድንጋይ ስንጥቅ ያለበት በመሆኑ ለዚህ ግዙፍ የሀብት ክምችት መፈጠር ምክንያት ሆኗል።  ምንም እንኳን ማዕድኑ የሚገኝበት ጥልቀት ለቁፋሮ ሥራ ፈታኝ ቢሆንም፣ የማዕድኑ ጥራት ግን የቁፋሮ ወጪውን ትርፋማ እንደሚያደርገው የታመነ ሲሆን፣ ግኝቱም ቻይና በዓለም ላይ ያላትን ቀዳሚ የወርቅ አምራችነት ደረጃ ይበልጥ እንደሚያጠናክርላት ይጠበቃል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories