በኢቢቪ ዘጋቢ
የኢትዮጵያን የሰነደ ሙዓለ ንዋች ገበያ ኢንቨስትመንት ምቹ እና ተደራሽ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀውን የመጀመሪያውን የድረ ገጽ እና የሞባይል ግብይት መተግበሪያ “ንዋይ” ማስጀመሩን ነው ያስታወቀው።
የሞባይል መተግበሪያው ገበያው ለግብይት አባላቱ ያዘጋጃቸውን የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ብሮከር ባክ ኦፊስ እና የትዕዛዝ አስተዳደር ሥርዓት በማቀናጀት፣ ደንበኛን ማስመዝገብ፣ ትዕዛዝ ማስተዳደር፣ ግብይት መፈጸም እና ሪፖርት ማቅረብን ጨምሮ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አገናኝነት ሥራዎችን ያቀላጥፋለል ተብሏል፡፡
መተግበሪያው ተጠቃሚዎች የገበያ ሂደቶችን መከታተል፣ የአክሲዮንና የዕዳ ሰነዶች ግብይቶችን በደህንነትና በብቃት መፈጸም እንዲሁም የፖርትፎሊዮዎቻቸውን አፈጻጸም በየሰዓቱ መከታተል እንደሚያስችላቸው ተጠቁሟል።
የገበያ ተደራሽነትን የሚገድቡ እንቅፋቶችን እና የግብይት ወጪዎችን በመቀነስ፣ ንዋይ መተግበሪያ የገበያ ተሰትፎን በማስፋት የኢትዮጵያን የፋይናንስ ሥነ-ምህዳር ያጠናክራል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን እስማኤል(ዶ/ር) እንደገለጹት ‘ንዋይ’ መተግበሪያ ኢንቨስተሮች በማንኛውም ጊዜና በማንኛውም ቦታ ገበያውን ማግኘት ያስችላቸዋል።
ገበያውን ተደራሽ በማድረግ፣ የካፒታል ገበያ ተሳትፎን ይበልጥ ሁሉን አቀፍ፣ ግልጽና ቀልጣፋ እያደረግን፣ ህብረተሰቡ በአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ በገበያ ውስጥ እንዲሳተፍ ያበረታታል ብለዋል፡፡
የቴክኖሎጂው ጥቅም ላይ መዋል የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያው አገናኝ አባላት ሚናቸውን አንዲወጡ ያግዛል ባለሀብቶች ደግሞ ያልተቋረጠ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የገበያ ተደራሽነትን እንዲያገኙ እንደሚያስችል ተናግረዋል።@SECO


