የአሉሚኒየም ዋጋ በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት ምክንያት የከፍተኛ ጭማሪ አሳየ

በመካከለኛው ምስራቅ በእስራኤል፣ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት የዓለም አቀፉ የአሉሚኒየም ገበያ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ወድቋል። በተለይም ስልታዊ ጠቀሜታ ያለው የሆርሙዝ የባህር መስመር ለጭነት መዘጋቱ፣ ከፋርስ ባሕረ ሰላጤ የሚወጣውን የማዕድን ምርት ሙሉ በሙሉ አግዶታል።

በዚህም ምክንያት በለንደን የብረት ገበያ (LME) የአሉሚኒየም ዋጋ በአንድ ሳምንት ውስጥ የ9.7% ጭማሪ በማሳየት፣ እ.ኤ.አ. ከ2023 ወዲህ ከፍተኛ የተባለውን የዋጋ ንረት አስመዝግቧል። ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ ይህ መስተጓጎል የሚቀጥል ከሆነ የአንድ ቶን አሉሚኒየም ዋጋ ከ$4,000 በላይ ሊያሻቅብ ይችላል።

በሌላ በኩል፣ የዓለም የወርቅ ገበያ መጠነኛ መረጋጋት እያሳየ ይገኛል። የወርቅ ዋጋ በአውንስ $5,174.59 በመድረስ ቀደም ሲል የነበረውን የሳምንት ቅናሽ አሻሽሏል። ለዚህም በዋናነት የአሜሪካ የሥራ ቅጥር መረጃ መውጣቱን ተከትሎ የፌዴራል ሪዘርቭ ባንክ የወለድ ምጣኔን ይቀንሳል የሚለው ተስፋ ምክንያት ሆኗል።

በተጓዳኝም የቻይና ማዕከላዊ ባንክ የወርቅ ክምችቱን ለ16 ተከታታይ ወራት በማሳደግ፣ አጠቃላይ የክምችት መጠኑን 387.59 ቢሊዮን ዶላር አድርሶታል።

በአሜሪካ በኩል ደግሞ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከቬንዙዌላ ጋር አዲስ የንግድ ግንኙነት ለመጀመር ፍላጎት ማሳየታቸው፣ ዋሽንግተን የሀገሪቱን የነዳጅ እና የማዕድን ሃብት ለመቆጣጠር እየሞከረች ነው የሚል ትችት አስነስቷል።

በቴክኖሎጂው ዘርፍ ደግሞ የጀርመኑ ቮልስዋገን በባትሪ ማዕድናት (እንደ ሊቲየም እና ኒኬል ያሉ) ላይ የሚያወጣውን ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ በማሳደግ የአሜሪካውን ቴስላ (Tesla) በመብለጥ ቀዳሚ መሆን ችሏል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories