በአፍሪካ የክሪፕቶ ምንዛሬ አጠቃቀም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑ ተገለፀ

ኢትዮጵያ በክሪፕቶ ምንዛሬ አጠቃቀም በዓለም 26ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች

በአፍሪካ የክሪፕቶ ምንዛሬ አጠቃቀም ካለፉት ዓመታት በበለጠ ፍጥነት እያደገ መሆኑን አዳዲስ መረጃዎች አመለከቱ።

በተለይም ከሐምሌ 2024 እስከ ሰኔ 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የ205 ቢሊዮን ዶላር ግብይት የተፈጸመ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ52 በመቶ እድገት አሳይቷል።

ናይጄሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በክሪፕቶ ምንዛሬ አጠቃቀም ቀዳሚዋ ሀገር ሆናለች። በጥናት ከተሳተፉት ናይጄሪያውያን መካከል 73 በመቶ የሚሆኑት የዲጂታል ምንዛሬ ባለቤት መሆናቸውን ወይም ተጠቅመው እንደሚያውቁ ገልጸዋል።

 ለዚህም እንደ ዋና ምክንያት የተጠቀሰው የናይጄሪያ ናይራ የመግዛት አቅም መዳከም እና ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት መከሰቱ ነው።

ደቡብ አፍሪካ በበኩሏ በዓለም 30ኛ ደረጃ ላይ ብትቀመጥም፣ ይበልጥ የዳበረ የክሪፕቶ የኢንቨስትመንት መዋቅር በመዘርጋት ትታወቃለች።

 በተለይም ተቋማዊ ባለሀብቶች በዘርፉ በስፋት እየተሳተፉ መሆኑ ገበያውን ይበልጥ የተረጋጋ እንዲሆን አድርጎታል።

በምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያ በክሪፕቶ ምንዛሬ አጠቃቀም በዓለም 26ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረገች መሆኑ ተመላክቷል። ኬንያ (28ኛ) እና ኡጋንዳ (በመጀመሪያዎቹ 30 ሀገራት ውስጥ) ተጠቃሽ የሆኑ ውጤቶችን እያስመዘገቡ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ ያለው ዝቅተኛ የባንክ ተደራሽነት፣ ህዝቡ አማራጭ የፋይናንስ አገልግሎቶችን እንዲፈልግ ማድረጉ ለዘርፉ እድገት አስተዋጽኦ እንዳበረከተ ዘገባው ያመለክታል።

ምንም እንኳን ቢትኮይን (Bitcoin) በስፋት ቢታወቅም፣ በአፍሪካ ውስጥ እንደ USDT እና USDC ያሉ ከዶላር ጋር የተሳሰሩና ዋጋቸው የማይዋዥቅ (Stablecoins) ምንዛሬዎች ይበልጥ ተመራጭ እየሆኑ መጥተዋል። እነዚህ ምንዛሬዎች በተለይ ለንግድ ክፍያ እና ለቁጠባ አገልግሎት በስፋት እየዋሉ ይገኛሉ።

በአፍሪካ ለክሪፕቶ ምንዛሬ መስፋፋት እንደ ዋና ምክንያት የቀረቡት የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና የዋጋ ግሽበትና የሀገር ውስጥ ገንዘብ የመግዛት አቅም ሲቀንስ ዜጎች ሀብታቸውን ለማቆየት ክሪፕቶን እንደ አማራጭ መጠቀማቸው እንደሆነ ተገልጿል።

ቀደም ሲል በርካታ የአፍሪካ ሀገራት በክሪፕቶ ምንዛሬ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ያደርጉ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ዘርፉን በህግ ማዕቀፍ ውስጥ ለማስገባትና የብሔራዊ ብሎክቼይን ፖሊሲዎችን ለመቅረጽ እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ተገልጿል።

ይህም በዘርፉ የሚታዩ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከልና የተጠቃሚዎችን መብት ለማስጠበቅ ይረዳል ተብሏል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories