በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ተደረገ
የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
በሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎት የተደረገው ጭማሪ ከአምስት እስከ 20 ብር ሲሆን በአዲሱ ተመን ከፍተኛ ጭማሪ የተደረገው የከተማ አውቶብስ ዋጋ ላይ ሲሆን ከፍተኛው የባስ ታሪፍ ከ50 ወደ 70 ብር ከፍ ብሏል።

የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ያወጣው ታሪፍ እንደሚያሳየው እስከ 2.5 ኪሎ ሜትር ሲከፈልበት ነበረው የ10 ብር ተመን ባለበት እንዲቀጥል ሲደረግ እስከ አምስት ኪሎ ሜትር የሚደረግ ጉዞ ደግሞ ከነበረበት 15 ብር ወደ 20 ብር ከፍ ብሏል።
እስከ 15 ኪሎ ሜትር ለሚደርሱ ጉዞዎች የተዘጋጁ የታሪፍ ተመኖች በተመሳሳይ የአምስት ብር ጭማሪ ተደርጎባቸዋል።
አዲሱ የታሪፍ ጭማሪ ከነገ መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ቢሮው አስታውል፡፡@SECO


