በኢቢቪ ዘጋቢ
የራሴ መርከቦች 409 ሺ ቶን ጭንት አጓጓዙ ሲል ግዙፉ የመርከብ አንቀሳቃሽ የኢትዮጵያ ባህር ትራነስፖርት እና ሎጅስቲክስ (ኢባትሎ) አስታወቀ።
9 ሁለገብ ጭነት የሚይዙ ነስተኛ እና አንድ ብትን ጭነት የሚሸከም መካከለኛ መርከቦች ያሉት ኢባትሎ በ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ግማሽ 409 ሺ 604 ቶን ጭነት በራሱ መርከቦች በማጓጓዝ “ለኢትዮጵያ አሌንታ መሆኔን ቀጥያለው፣” ሲል ባወጣው መረጃ ጠቅሷል።
በወቅቱ ያጓጓዘው ጭነት ከአምና ተመሳሳይ ወቅት በ50 በመቶ ከእቅዱ ደግሞ 61 በመቶ ብልጫ ያለው ነው።
ከሳምንታት በፊት የእባትሎ ዋና ስራ አስፈፃሚ አብዱልበር ሸምሱ የድረጅታቸው መርከቦች የኢትዮጵያ ጭነት በማጓጓዝ ላይ ትኩረት መስጠታቸውን ገልፀው ነበር።

በአፍሪካ ርቀት የሚጓዝ ብቸኛ የመርከብ አንቀሳቃሽ እንደሆነ የሚጠቀሰው ኢባትሎ በ5 አመት እቅዱ 6 ተጨማሪ መካከለኛ ሚባሉትን አይነት መርከቦች ለመግዛት አቅዷል።
ከነዚህ መካከል ከ3 እስከ 5 ሺ 20 ጫማ ኮንቴነር የሚይዝ ያገለገለ አንድ የኮንቴነር መርከብ።
በተጨማሪ 3 እስከ 8 አመት ብቻ ያገለገሉ 65 ሺ ቶን ገደማ የመጫን አቅም ያላቸው አልትራማክስ ሁለገብ መርከቦች የመግዛት እቅድ ነው የያዘው።
ድርጅቱ በቅርቡ ከልሶ ባወጣው ጨረታ ሁለት ሁለገብ አልትራማክስ መርከቦችን ማስገንባት ይፈልጋል።
ለግዥው ግማሹን እራሴ ቀሪውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲያበድረኝ እየተደራደርኩ ነው ብሏል።
ቀደም ሲል ለመርከቦቹ ግዥ ከንግድ ባንክ በተጨማሪ ዳሽን እና አዋሽ ባንኮች ብድር እንዲያመቻቹ ኢባትሎ ሲነጋገር እንደነበር ይታወሳል።
ሆኖም በቅርቡ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለጋዜጠኞች የሰጡት ዋና ስራ አስፈፃሚው የብድር ድርድሩ ከንግድ ባንክ ጋር ብቻ ሆኗል ብለዋል።©SECO


