በሀብት መጠኑ የኬንያ ግዙፉ የንግድ ባንክ የሆነው ኬሲቢ ግሩፕ (KCB Group)፣ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለመግባት የሚያደርገውን ዝግጅት አጠናክሮ በመቀጠል የሚገዛውን አንድ የሀገር ውስጥ ባንክ መለየቱን በይፋ አስታውቋል።
ባንኩ ይህንን እርምጃ የወሰደው እ.ኤ.አ. በ2025 የ68.4 ቢሊዮን የኬንያ ሽልንግ (544 ሚሊዮን ዶላር) ሪከርድ ትርፍ ማስመዝገቡን ተከትሎ ሲሆን፣ ይህም በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ የሚያስችል ጠንካራ የፋይናንስ አቅም ሰጥቶታል።
ኬሲቢ አዲስ ባንክ ከመክፈት ይልቅ ቀድሞ የነበረን የሀገር ውስጥ ባንክ በመግዛት ወደ ገበያው ለመግባት የመረጠ ሲሆን፣ ይህም የባንኩን የደንበኞች መሠረትና የቅርንጫፍ መረብ በቀጥታ ለመጠቀም ያስችለዋል።
ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ሕግ ለውጭ ባለሀብቶች የባለቤትነት ገደብ ቢያስቀምጥም፣ ኬሲቢ ግን በልዩ ሁኔታ የባንኩን “አብላጫ ቁጥጥር” ለመረከብ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።
በተጨማሪም ባንኩ በኢትዮጵያ ሰፊ የቅርንጫፍ ግንባታ ወጪን ለማስቀረት፣ እንደ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሁሉ በዲጂታልና በሞባይል ባንክ አገልግሎቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ደንበኞችን ለመድረስ አቅዷል። ግሩፑ የሚገዛውን ባንክ በይፋ በዚህ ዓመት እንደሚያሳውቅና አጠቃላይ ሂደቱን እስከ 2026 ማብቂያ ድረስ አጠናቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ይጠበቃል። በአሁኑ ወቅት እንደ ስታንዳርድ ባንክ እና አብሳ ግሩፕ ያሉ ሌሎች የአፍሪካ ግዙፍ ባንኮችም የ120 ሚሊዮን ሕዝብ ያላትን የኢትዮጵያ ገበያ ለመቀላቀል ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።@SECO


