የኢትዮጵያ አየር መንገድ እ.ኤ.አ እስከ 2032 ድረስ ያለውን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ በዚህም ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹን ወደ 242 ለማድረስ መታቀዱ ተገልጿል።
ይህ ማስታወቂያ የተሰማው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የአየር መንገዱን የሥራ እንቅስቃሴ በጎበኙበት ወቅት ነው። ፕሬዚዳንቱ አየር መንገዱ የሀገር ምልክት መሆኑን ጠቅሰው፣ ተቋሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ተወዳዳሪነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚያደርገውን ጥረት እንዲቀጥል አሳስበዋል።
የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በበኩላቸው፣ አየር መንገዱ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹን በማስፋት የአፍሪካ ግዙፍ አየር መንገድነቱን ለማስቀጠል በትጋት እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።@SECO


