የብር የመግዛት አቅም በሁለት ሳምንት ውስጥ በ አንድ በመቶ ተዳከመ

የባንኮች ፍላጎት ለጨረታ ከቀረበው የውጭ ምንዛሬ በሁለት እጥፍ ተኩል የላቀ ሆኗል

የትይዩ ገበያ ዋጋ እየተዳከመ ነው ቢሆንም የባንኮች የውጭ ምንዛሬ የመግዛት ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑ እየተገለጸ ነው፡፡

ዛሬ በተደረገው መደበኛ ጨረታ የብሄራዊ ባንክ 70 ሚሊየን ዶላር ለመሸጥ ያወጣ ቢሆንም የተሳተፉት 30 ባንኮች በጥቅሉ 241.5  ሚሊየን ዶላር ለመግዛት መፈለጋቸው ታውቋል፡፡

በተጨማሪ አንድን ዶላር ለመግዛት የቀረበው የብር መጠን 158.5 ብር ሲሆን ይህም ከቀዳሚው ጨረታ የ2.5 ብር ወይም የ1.6 በመቶ ጭማሪ የታየበት ነው፡፡

አማካኝ ጨረታውን ያሸነፈው ዋጋ 157.46 ብር ለአንድ ዶላር ሲሆን ይህም ከሁለት ሳምንት በፊት ከተደረገው ጨረታ አንፃር የአንድ በመቶ የብር መዳከም የታየበት ነው፡፡

በጨረታው 9 ባንኮች የቀረበውን የውጭ ምንዛሬ ተከፋፍለዋል፡፡ ይህም ለአንድ ባንክ በአማካኝ 7.7 ሚሊየን ዶላር ገደማ ደርሶታል ማለት ነው፡፡

ከባህረሰላጤው ግጭት ጋር ይሁን አይሁን ባልተወቀ መልኩ የጥቁር ገበያ ከሰሞኑ መቀዛቀዝ እያሳየ ነው፡፡ በተመሳሳይ ብሄራዊ ባንክ ጠንካራ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑ ይታወሳል፡፡@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories