ባለስልጣኑ የነዳጅ አቅርቦትን ለመጠበቅ አዲስ የቅድሚያ ተጠቃሚነትና የቁጠባ መመሪያ አውጥቷል
ባለሥልጣኑ ዛሬ መጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣውና ለነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች ባሰራጨው መመሪያ የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች፣ የነዳጅ ቸርቻሪ ማደያዎች በየደረጃው ተቆጣጣሪ ተቋማት በኃላፊነት ማሳሰቢያውን መተግበር እንደሚጠበቅባቸው ያስታወቀው ባለስላጣኑ የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎችና በስራቸው የሚገኙ ማደያዎች በኃላፊነት የወጣውን መመሪያ እንዲተገብሩ አስጠንቅቋል፡፡
ነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች ማንኛውንም የነዳጅ ጭነት በሚመለከት በቅድሚያ ለጸጥታ ተቋማት እና ቁልፍ የሆነ የመንግስት ፕሮጀክቶችን በተለይም በመጠናቀቅ ላይ ያሉ የልማት ሥራዎችን ቅድሚያ መስጠት እንዲሁም ኢንዱስትሪዎች እና መሠረታዊ ሸቀጦችን ለሚያመርቱ አምራች ድርጅቶች እና ወደ ውጭ አገር የሚልኩ ታላላቅ የቀጥታ ተጠቃሚዎች ቅድሚያ በመስጠት ማሰራጨት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በተፈቀደላቸው ቦታ እና በተቀመጠላቸው የመድረሻ ጊዜ (Timing Arrival) መሠረት ወደ መዳረሻ ቦታቸጡ መድረሳቸውን ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው አስታውቋል፡፡
ነዳጅ ቸርቻሪ ማደያዎች ለህዝብ ትራንስፖርት ለሚሰጡ ተሸከርካሪዎች ቅድሚያ በመስጠት፣ ማንኛውም ተሽከርካሪ በፋብሪካው ከተገጠመለት ሰልቫቲዮ ውጭ ተጨማሪ ሳልቫቲዮ አስገጥሞ ነዳጅ ለመቀዳት የሚመጣ ማንኛውም አሽከርካሪ ካጋጠማችሁ ማስተናገድ እንደሌለባችሁ እና በአቅራቢያችሁ ለሚገኝ የፀጥታ አካላት መጠቆም እንዳለባቸው ባለስላጣኑ አስታውቋል፡፡@SECO


