የፓን-አፍሪካየሥነ-ፈጠራ ኢኮኖሚ እና የኢኖቬሽን ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ

በፌስቲቫ ከ10 ሺህ ሰዎች በላይ እንደሚታደሙ ተጠቁሟል፡፡

የሥነ-ፈጠራ ጥበባት ለለውጥ  በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ፣ በዘሌማን ኮሚኒኬሽን እና በፍሎውለስ ኤቨንትስ ትብብር የሚዘጋጀው ፌስቲቫል  የአፍሪካን የሥነ-ፈጠራ ኢንዱስትሪ ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ አቅም መቀየርን ቀዳሚ ዓላማው እንደሆነ ተነገሯል፡፡

ክራፍት አዲስ ሥነ-ፈጠራ ከካፒታል ጋር የሚገናኝበት ልዩ ፓን-አፍሪካዊ መድረክ እንደሆነም ተጠቁሟል።

ፌስቲቫሉ  ሥራ ፈጣሪዎች፣ ባለሀብቶች ፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች እና ባለድርሻ አካላትን በማገናኘት የአፍሪካ የሥነ-ፈጠራ ኢንዱስትሪ ያለውን ሙሉ የኢኮኖሚ አቅም ለመጠቀም ያስችላል ተብሏል።

 ከመደበኛ የተሰጥኦ ትርኢቶች እና  የፌስቲቫል ክንውኖች ባሻገር በሥራዎች ዕድገት፣ በገበያ ተደራሽነት እና በዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ተገልጿል።

መድረኩ የአፍሪካ የሥነ-ፈጠራ ውጤቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና እንዲኖራቸው እና ስራቸውን  በስፋት ለማሰራጨት እንዲሁም ለማሳደግ የሚያስችላቸውን እድል እንደሚፈጥር ነው አዘጋጆቹ የተናገሩት፡፡

የሥነ-ፈጠራ ዘርፍ ለሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት (GDP) ትልቅ አስተዋጽኦ ካላቸው እና ለወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል ከሚፈጥሩ ዘርፎች መካከል አንዱ ሲሆን ለአህጉሪቱ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ መሪ ኃይል ነው ተብሏል፡፡

ፌስቲቫሉ ከሚያዝያ 22 እስከ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በአድዋ ድል መታሰቢያ የሚካሄድ ሲሆን ከ10 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚታደሙና  በኢንቨስትመንትና በሥነ-ፈጠራ ኢኮኖሚ ዙሪያ የተለያዩ የፓናል ውይይቶች እንደሚካሄድ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪና የኢትዮ-ጃዝ ሙዚቃ አባት በሆነው ሙላቱ አስታጥቄ ‘የክብር ኮንሰርት’   እንደሚቀርብ አዘጋጆቹ ጨምረው ገልጸዋል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories