አማራ ባንክ  ከፍተኛ ልምድ ያላቸውን አመራሮች በሥራ አስፈጻሚነት መመደቡን አስታወቀ

ሹመቱም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መጽደቁ ታውቋል፡፡

አማራ ባንክ የባንኩን የአምስት ዓመት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በላቀ ደረጃ ለማሳካትና ተወዳዳሪነቱን ለማጠናከር፣ በብቃታቸውና በሥራ ልምዳቸው የተመሰከረላቸው የማኔጅመንት አባላትን በቁልፍ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ መመደቡን ገልጿል።

የአመራር ምደባው የባንኩን ዕድገት ለማፋጠን፣ የአገልግሎት አቅሙን ለማሳደግና በፋይናንስ ዘርፉ ውስጥ ያለውን ድርሻ ለማጎልበት ታስቦ የተከናወነ ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ ባንኩ አስታውቋል።

ባንኩ አዲስ የሥራ አስፈጻሚ አባላትን ከነባር ከፍተኛ አመራሮች ጋር በማሰባጠር፣ የባንኩን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና የረጅም ጊዜ ራዕይ በብቃት ለመምራት የሚያስችል ማኔጅመንት ማዋቀሩን ጠቁሞ በዚህም አቶ ሳሙኤል ታደሰ ቺፍ ሪቴል ባንኪንግ ኦፊሰር እና ተ/ዋና ሥራ አስፈፃሚ፣ አቶ እሸቴ የማታ ቺፍ ኮርፖሬት ባንኪንግ ቢዝነስ ኦፊሠር፣ አቶ መንግስቱ ኃይሉ ቺፍ ኮረፖሬት ሰፖርት ሰርቪስ ኦፊሠር፣ አቶ በኃይሉ ጉልላት ቺፍ ባንኪንግ ኦፕሬሽንስ ኦፊሠር እንዲሁም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና የዲጂታል ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሠሮች ሆነው ሲሾሙ ሹመታቸውም  በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መጽደቁ ቅዳሜ ገበያ ከባንኩ ያገኘችው መረጃ ያሳያል፡:@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories