በአለምሰገድ እስጢፋኖስ
ኢትዮ ቴሌኮም፣ ከኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ጋር በመተባበር ዘመናዊ የዲጂታል የክፍያ ሥርዓት በዛሬው ዕለት ተግባራዊ አድርጓል።
የአዲስ አበባ – አዳማ የፈጣን መንገድ ላይ የሚሰጡ የመንገድ አገልግሎት ክፍያዎችን፣ የቅጣት ክፍያዎችን መፈጸም የሚያስችል ቶሎ (TOLO) የተሰኘና በቴሌብር ሱፐር አፕ ላይ የተመሠረተ የሂሳብ መሙያ ሚኒ አፕ እንደሆነ ተገልጿል።

አዲሱ የአገልግሎት እና የቅጣት ክፍያ አስተዳደር ሥርዓት ቀደም ሲል የነበረውን በእጅ የሚከናወን አሠራር ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ የአውቶሜሽን አሠራር የሚተካና በቴሌብር ሱፐር አፕ ውስጥ የሚገኘውን በ RFID ሲስተም በመታገዝ TOLO Mini App ክፍያዎችን በራስ-አገዝ ቴክኖሎጂ ተቀናሽ በማድረግ ተሽከርካሪዎች ለክፍያ ሳይቆሙ በቀጥታ እንዲያልፉ ያስችላል ተብሏል።SECO


