በሞጆ ከተማ በግራንዴር ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተገነባው ፋብሪካ፣ መሰረት ልማቱ በ300,000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ፣ የዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ የሴራሚክና የፖርሲሌን ንጣፎች ማምረቻ ፋብሪካ ነው።
በአሁኑ ወቅት 60×60 የሴራሚክ ንጣፎችን በስፋት ማምረት የጀመረው ይህ ፋብሪካ፤ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ የምርት ዓይነቶቹን በማስፋት የ80×80፣ 60×120፣ 70×140 እና 80×160 መጠን ያላቸውን የንጣፍ ዓይነቶች እንዲሁም የአውሮፓን የጥራት ደረጃ ያሟሉ የፖርሲሌን ምርቶችን ማቅረብ እንደሚጀምር ይጠበቃል።
ለግንባታው ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጥቶበታል፡፡ ፋብሪካው ከውጭ አገር የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት አይነተኛ ሚና አለው ተብሏል፡፡@seco


