የአፍሪካ ልማት ባንክ ይፋ ባደረገው የ”2026 የአፍሪካ ኢኮኖሚ ትንበያ” ሪፖርት መሰረት፣ የአፍሪካ ኢኮኖሚ በ2026 በ4.2 በመቶ እንደሚያድግ ታውቋል። ይህ እድገት በ2025 ከነበረው 4.4 በመቶ መጠነኛ ቅናሽ የሚያሳይ ቢሆንም፣ በ2027 ወደ 4.4 በመቶ እንደሚመለስ ትንበያው ይጠቁማል።
ሪፖርቱ አፍሪካ በአለም አቀፍ የጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች እና የኢኮኖሚ ተግዳሮቶች መካከል ጠንካራ የመቋቋም አቅም እንዳሳየች ገልጿል። ይሁን እንጂ አህጉሪቱ ለዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት ከ1.3 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የፋይናንስ ክፍተት እንዳለባት ባንኩ አስታውቋል። ይህንን ክፍተት ለመሙላት የሀገር ውስጥ ሃብትን በአግባቡ ማሰባሰብ እና የካፒታል ፍሰትን ውጤታማ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን በሪፖርቱ ተመላክቷል።@seco


