በኢቢቪ ዘጋቢ
በምርጫው ሂደት ላይ የምርጫ ቦርድ፣ እጩዎች እና የሲቪል ማህበራት ያደረጉትን ጥረት አድንቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ እና የአባል አገራቱ ኤምባሲዎች፣ ከካናዳ፣ ኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ጋር በመተባበር በጋራ ባወጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ምርጫ መካሄዱን አድንቀዋል፡፡
ቡድኑ በመግለጫው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎች እና የሲቪል ማህበራት በምርጫው ሂደት ላይ ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግኗል።
የአፍሪካ ህብረት እና ኢጋድ እንደ አለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች ያላቸውን ሚና ጠቅሶ የመጨረሻ ሪፖርታቸውን በጉጉት እንደሚጠብቅ ገልጿል።
እንዲሁም ግንቦት 24 ምርጫ ማካሄድ ያልቻሉ ክልሎች በቀጣይ ዕድል እንደሚያገኙ ተስፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
በሌላ በኩል የእንግሊዝ ኤምባሲ በኢትዮጵያ በምርጫ ማካሄድ በተቻለባቸው አካባቢዎች የመርጫ ሂደቱ በሰላም መጠናቀቁን አመስግኗል።
ኤምባሲው እጩዎችን፣ የሲቪል ማህበራት ታዛቢዎችን፣ በጎ ፈቃደኞችን እና የምርጫ ቦርድን ጨምሮ ምርጫው እንዲሳካ ላደረጉት ጥረት አድናቆትን ችሯል። ኤምባሲው አፍሪካ ህብረት እና ኢጋድ በምርጫው ያደረጉትን የክትትል ሪፖርታቸውን እንደሚጠብቅ አስታውቋል።@seco


