ዘምዘም ባንክ የአክሲዮን ምዝገባ ማፅደቂያ ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በማግኘት የመጀመሪያዉ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ ባንክ ሆነ

በዓለምሰገድ እስጢፋኖስ


ዘምዘም ባንክ ከግብይት አማካሪው ከወጋገን ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር በመሆን በዛሬው ዕለት እያ ሆቴል በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተገለጸው


በኢትዮጵያ የባንክ ኢንደስትሪ የመጀመሪያ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ ባንክ በመሆን የዛሬ 5 ዓመት ወደ ስራ የገባው ዘምዘም ባንክ ያሉትን ነባር አምስት ሚልዮን አክስዮኖች ዋጋቸዉ አምስት ቢልዮን የሆኑ እና ተጨማሪ አንድ ሚልዮን አክስዮኖች ዋጋቸዉ አንድ ቢልዮን የሆነ በትርፍ ድርሻ ወደ ካፒታል የሚቀየር እና በቅድሚያ መብት አክስዮን ማሳደግ የያዘ የምዝገባ መግለጫ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ECMA) ጸድቋል፡፡


ባንከኩ በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ የመጀመሪያው ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ ባንክ በመሆን በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሰልጣን በመመዝገብ እና አክሲዮኖቹን መሸጥ የሚችልበትን ዕድል በመፍጠር ረገድ ቀዳሚ እንደሚያደርገው ተነግሯል።


ባንኩ ይህንን ይፋዊ ምዝገባ ያረጋገጠው ሰነደ ሙዓለ-ንዋይን ለሕዝብ የማቅረብ እና የግብይት መመሪያ በሙሉ ብቃት በማሟላት ነባር አክሲዮኖቹን የመመዝገብ እንዲሁም ካፒታሉን ለማሳደግ ዓይነተኛ ዕመርታ የሚፈጥርለትን ፍቃድ ለማግኘት እንደቻለ አስታውቋል፡፡

ዘምዘም ባንክ ያገኘው ፈቃድ አክሲዮኖቹን በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በኩል ለህዝብ እንዲደርሱ በማድረግ ህጋዊ’ ቀልጣፋ እና አስተማማኝ ግብይት እንዲኖር ከማስቻሉም በላይ፣ ለኢንዱስትሪው መስፋፋትና ዕድገት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተጠቁሟል፡፡@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories