በአለማችን እጅግ ውድ የሚባለው የከበረ ድንጋይ ኢትዮጵያ ተገኝቷል

በ1980ዎቹ በብራዚል ፓሪባ ግዛት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተገኘ የተገለፀው ፓሪባ እጅግ ብርቅ ድንጋይ በኢትዮጵያ መገኘቱ ነው የተሰማው።

ከብራዚል በተጨማሪ በ2000ዎቹ መጀመሪያ በናይጄሪያ እና ሞዛምቢክ እጅግ በጥቂቱ ሞኖሩ የተረጋገጠው ጥቅሙ የላቀ እንዲሁም እንደ አልማዝ ካሉ የከበሩ ድንጋዮች የበለጠ ዋጋ ያለው መሆኑ ታውቋል።

የቅዳሜ ገበያ ምንጮች ይህ እጅግ ውድ ድንጋይ በኢትዮጵያ መኖሩ ታውቆ መሸጥ ከተጀመረ ቆየት ብሏል የሚል መረጃ ነው የጠቀሱት።  

ስለ እንቁው መኖር ግን መንግስት በቂ እውቀት የለው ያሉ ሲሆን መሰል ሁኔታ በሌሎች አዳዲስ መአድናት ወይም ማውጫ ቦታዎች ሲከሰት ቆይቷል ነው ያሉት።

ከሳምንት በፊት የስዊዘርላንድ ጂኦሎጂካል ተቋም ከየት አገር እንደ መጣ የማይታወቅ ፓሪባ ድንጋይ ለፍተሻ መጥቶለት እንደነበር መጥቀሱ ግን አሁን ጉዳዩ ትኩረት ስቦ ዘርፉን በሚከታተሉ ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል ነው የተባለው፡፡

የስዊዘርላንዱ ላብራቶሪ ባወጣው መግለጫ ድንጋዩ ከብራዚል የሚመጣው አይነት እንሰሚመስል ነገር ግን አፈጣጠሩ ከብራዚል አለመሆኑን በፍተሻ ወቅት ማረጋገጡን ነው ያስታወቀው።

ባወጣው መግለጫ ጨምሮ እንዳስረዳው አዲሱ የብርቅ ድንጋይ ምንጭ ኢትዮጵያ ሳይሆን አይቀርም ነው ያለው፡፡

ከስዊዘርላንድ የወጣው መረጃ ለውዱ ጌጥ መኖር ማረጋገጫ ካልሆነ በስተቀር ፓሪባ በኢትዮጵያ ደቡባዊ ክፍል  ቦረና አካባቢ ከጥቂት አመታት በፊት የድንጋዩን ምንነት በለዩ ሰዎች አማካኝነት እየወጣ መንግስት ሳያውቀው መሸጥ መጀመሩን ለጉዳዩ ቅርበት አለን የሚሉ አካላት ቅዳሜ ገበያ የተናገሩት።

ነገር ግን በማእድን ምንነት ምርመራ በአለም ላይ ከፍተኛ ግምት በሚሰጠው የስዊዘርላድ የፍተሻ ላብራቶሪ ሁኔታው ይፋ መደረጉ ነገሩ እንደ አዲስ እንዲራገብ አድርጎታል ይላሉ፡፡

አሁን ላይ ዋናዋ የፓሪባ የከበረ ድንጋይ አቅራቢ ሞዛምቢክ ናት ተብሏል።

#ቅዳሜገበያ #etbusinessview #ethiopia #pariba #mining #Switzerland

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories